የከምባታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት የጽ/መሣሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች (ሎት 1)፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ሎት 2)፣ ፈርኒቸር (ሎት 3) እና ሞተር ሳይክሎች (ሎት 4) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የከምባታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት የጽ/መሣሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች (ሎት 1)፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ሎት 2)፣ ፈርኒቸር (ሎት 3) እና ሞተር ሳይክሎች (ሎት 4) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 13, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ግዥ መለያ ቁጥር 001/2019 ከዞፋመ

የከምባታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ሴ/መ/ቤቶች የዕቃ ግዥ በጥቅል በሎት አደራጅቶ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፦

  1. LOT የጽ/መሣሪያና ሌሎች አላቂ
  2. LOT 2 የኤሌክትሮኒክስ
  3. LOT 3 ፈርኒቸር
  4. LOT-4 ሞተር ሳይክሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፦

1.ተጫራቾች በመስክ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላችሁ

2.የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆናችሁ፤

3.በዘርፉ የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ፣

4. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ የሚችል ሆኖ መ/ቤቱ ቀድሞ ናሙና እንዲቀርብ በሚፈልግ ወቅት ለመቅረብ ፈቃደኛ የሆነ የሚያቀርበው የተጫራቹ ዋጋ ጨረታ ከተከፈተበት ቀን አንስቶ ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፣

5.ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር ማቅረብ የሚችል፣

6.ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከምባታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በማቅረብ መግዘት ይቻላል።

7.ተጫራቾች የጨረታው ዋጋ አንድ ኦርጂናልና ኮፒ በፖስታ አሽገው ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን በ11ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በማቅረብ ታሽጎ በዚያው ዕለት 9፡30 ተጫራች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ግን ቀኑ በዓል የዕረፍት ቀናት ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

ማሳሰቢያ፡– መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፍል መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ 046-554-03600016 መደወል ይቻላል

ዱራሜ

የከምባታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *