በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በዩኒሴፍ በጀት በክልሉ ባሉት ወረዳዎች የጭነት አገልግሎት ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በዩኒሴፍ በጀት በክልሉ ባሉት ወረዳዎች የጭነት አገልግሎት ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 17, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 03/2019

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በዩኒሴፍ በጀት በክልሉ ባሉት ወረዳዎች የጭነት አገልግሎት ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም –

ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር መስፈርት መሰረት ለመሣተፍ የሚፈልጉ ፡

  1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለብሬ መሆን አለባቸው፤
  2. ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ር/ ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው፤
  3. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 -6:00 ድረስ ብቻ ለዚህ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፣ ሆኖም 11ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀስው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  5.  የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ90 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በሲፒኦ ወይም አንኮንዲሽናል የባንክ ዋስትና በማቅረብ መወዳደር አለባቸው፤
  6. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጊዜ አንድ ኮፒ እና ኦርጅናል ፖስታ በማሽግ ቴክኒካል፣ ፋይናንሻል የጨረታ ዶክመንት በአንድ ላይ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፤
  7. ጨረታው ለ3 ወራት /90 ቀናት ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡
  8. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ከግዥ ክፍል 14 ቁጥር ማግኘት ይቻላል፡
  9. ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡– ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 /ሀያ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነው ግዥ

50% ቫት ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046-221- 70-02/03

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

ሀዋሳ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *