በደ/ኢ/ህ/ክ/መንግስት በወላይታ ዞን ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ፕላን ልማት ዩኒት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች ሥራ ጉዳይ የሚውል የተለያዩ ዓይነትና መጠን ያላቸውን ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደ/ኢ/ህ/ክ/መንግስት በወላይታ ዞን ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ፕላን ልማት ዩኒት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች ሥራ ጉዳይ የሚውል የተለያዩ ዓይነትና መጠን ያላቸውን ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 17, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ኢ/ህ/ክ/መንግስት በወላይታ ዞን ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ፕላን ልማት ዩኒት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች ሥራ ጉዳይ የሚውል የተለያዩ ዓይነትና መጠን ያላቸውን ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለምንፈልግ ከዚህ በታች በተዘረዘሩ ሎቶች መወዳደር ይችላሉ።

  • ሎት 1 አላቂና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች
  • ሎት 2 ተሽከርካሪ ወይም ሞተር ሳይክል
  • ሎት 3 የኤሌክትሮንክስ እቃዎች
  • ሎት 4 የአስተዳደር ሠራተኞች ደንብ ልብስ
  • ሎት 5 የህንፃ መሳሪያዎች ሲሆኑ ከላይ በተጠቀሱ ሎቶች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

የተጫራቾች መመሪያ፡–

1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ቲን ካርድ፣የንግድ ም/ም/ወረቀት፣አቅራቢነት ም/ም/ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሴርትፊኬት ማቅረብ የሚችል።

2. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ኦሪጅናልና ሁለት የኦሪጅናል ኮፒ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ሙሉ ስም፣ አድራሻ፤ፊርማ፣የሚወዳደሩበት ሎት እና የድርጅቱ ማህተም በትክክል ተደርጎ በሰም በታሸገ እንቨሎፕ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን መክተት ይኖርበታል።

3. ፖስታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቹ ራሱን ከጨረታ ማግለል አይችልም።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10,000 /አስር ሺህ /ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በCPO ማስያዝ ይኖርበታል።

5. የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 በገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ፕላን ልማት ዩኒት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ይከፈታል። ዕለቱ ሰንበት /በዓል/ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች በገዛ ፈቃዳቸው በጨረታ ቦታ ያለመገኘት የጨረታውን ሂደትአያስተጓጉልም።

6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስሪዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከገሱባ ከተማ አሰ/ር ፋ/ፕላን ልማት ዩኒት ግዥ ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላል።

8. ለአሸናፊው ተጫራች በደብዳቤ ከተገለፀ በሶስት ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ብቻ በማቅረብ ውል መዋዋል ይጠበቅበታል።

9. የጨረታ ማሰከበሪያ አሸናፊ ተጫራች እንደታወቀና ውል ከተፈራረመ በኋላ ለተሸናፊ ተጫራች ተመላሽ ይደረጋል።

10. አሸናፊ ተጫራች ዕቃውን እስከ ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ፕላን ልማት ዩኒት ግቢ አድርሶ ያስረክባል።

11. መ/ቤቱ የተሻለ ዜደ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 0935 448 792 / 0913 950 407 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።

አድራሻ፦ ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ፕላን ልማት ዩኒት

በደ/ኢት/ያ ክልል/መ/በወላይታ ዞን ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ፕላን ልማት ዩኒት