2merkato.com (Nov 21, 2026)
የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ (EOI) ጥሪ
የውጭ የሰው ኃይል አቅርቦት አገልግሎት ለምትሰጡ ብቁ ድርጅቶች የተዘጋጀ
(EXPRESSION OF INTEREST (EOI) FOR PROVISION OF OUTSOURCED HUMAN RESOURCES)
ይህ ሰነድ ይፋ የተደረገበት ቀን (Document Release Date)፡ ህዳር 12
የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ ምላሽ መቀበያ የመጨረሻ ቀን (Last Date for Receipt of EOI Responses)፡ ህዳር 25
1. መግቢያ (INTRODUCTION)
ሳፋሪኮም ቴሌኮምኒኬሽንስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ኩ (“ሳፋሪኮም”) ፈጠራ የታከለባቸው የቴሌኮምኒኬሽንና ዲጂታል አገልግሎቶችን ለማቅረብ ቁርጠኛ ሲሆን፣ የንግድ ሥራዎቹን፣ ስትራቴጂካዊ ዕቅዶቹን እና የፕሮጀክት አፈጻጸም ፍላጎቶቹን ለመደገፍ ብቁና ክህሎት ያለው የሰው ኃይል መኖሩን ያረጋግጣል።
ይህ የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ (EOI) በባለሙያዎች ምልመላ፣ ቅጥር፣ የውጭ የሰው ኃይል አቅርቦት (Workforce Outsourcing)፣ የሰው ኃይል ማጠናከሪያ (Resource Augmentation) እና በሙያዊ የሰው ኃይል አስተዳደር አገልግሎቶች ዘርፍ ልምድና ብቃት ያላቸውን ድርጅቶች ለመለየት ያለመ ነው። ሳፋሪኮም እየተለዋወጡ የሚመጡ የሥራ እና የአሠራር ፍላጎቶችን ለማሟላት በጊዜያዊነት፣ በኮንትራት፣ በፕሮጀክት ላይ የተመሠረተ፣ በውጭ አቅርቦት (Outsourced) ወይም በሚተዳደር አገልግሎት (Managed Service) መልክ ብቁ ባለሙያዎችን ማቅረብ የሚችሉ በቅድሚያ የተመረጡ አቅራቢዎችን (Prequalified Suppliers) ስብስብ ለማቋቋም አቅዷል።
2. ስለተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያው (THE EOI)
ይህ የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ (EOI) ለሳፋሪኮም ቴሌኮምኒኬሽንስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ኩ የባለሙያዎች ስብስብ አገልግሎት (Talent Pool Services) ማቅረብ የሚችሉ መልካም ስምና ብቃት ያላቸውን አቅራቢዎች ለመለየት ያለመ ነው። የተመረጡት አቅራቢዎች እንደየፍላጎቱ ብቁና ችሎታ ያላቸውን ባለሙያዎች በማቅረብ የሳፋሪኮምን የንግድና የሥራ ማስኬጃ ፍላጎቶች ይደግፋሉ። ዝርዝር የጨረታ ሰነዶች በዚህ የፍላጎት ማሳወቂያ ሂደት በቅድሚያ ተመርጠው ብቁ ለሆኑ (Shortlisted/Prequalified) ድርጅቶች ብቻ በቀጣይ በሚወጣው የፕሮፖዛል መጠየቂያ (RFP) ሂደት የሚላኩ ይሆናል።
3. የተጫራቾች መሠረታዊ መስፈርቶች (BASIC RESPONDENTS / BIDDERS REQUIREMENTS)
|
መስፈርቶች (Requirements)
|
ዝርዝር መግለጫ (Description)
|
|
ሕጋዊ አቋም
(Legal Status)
|
አቅራቢው በሕጋዊ መንገድ የተመዘገበ ድርጅት መሆን አለበት።
(የአቅራቢነት ምዝገባ ምሥክር ወረቀት መቅረብ አለበት)
|
|
ብቁነት
(Eligibility)
|
አቅራቢው በማናቸውም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN)፣
በዓለም ባንክ ቡድን (World Bank Group) ወይም በሌላ
በማናቸውም ዓለም አቀፍ ድርጅት ያልታገደ፣ ከጨረታ
ያልተከለከለ ወይም ብቁ አይደለም ተብሎ ያልተፈረጀ መሆኑን
ማረጋገጥ አለበት።
|
|
የአቅራቢው ምሥክር ወረቀቶችና ፈቃዶች
(Supplier Certificates and Licenses)
|
አቅራቢው በኢትዮጵያ በሚመለከተው የንግድ ሚኒስቴር
እና/ወይም የንግድ ምዝገባ አካል የተመዘገበ የአገር ውስጥ
ድርጅት ሊኖረው ይገባል። አቅራቢው ከአገር ውስጥ ባለሀብት
ወይም አቅራቢ ጋር በአጋርነት የሚሠራ የውጭ ባለሀብት ከሆነ፣
ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን (EIA) ሰነዶችን አቅርቦ
የንግድ ፈቃድ ለማውጣት የሚያስችል የኢንቨስትመንት ፈቃድ
ያገኘ መሆን አለበት። (አዎ ከሆነ፣ የታደሰውን ምሥክር ወረቀት
ቅጂ ያቅርቡ)
አቅራቢው በተጠቀሰው የሥራ ዘርፍ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ
ሊኖረው ይገባል።
|
|
ሁሉም የድርጅቱ ሰነዶች
(All Company Documents)
|
ለሚመለከታቸው አገልግሎቶች የተዘጋጀ ከሃያ አምስት (25) ገጾች
ያልበለጠ የድርጅቱ መገለጫ (Company Profile)።
አግባብነት ያለው የንግድ ሥራና የንግድ ምዝገባ ፈቃድ።
አቅራቢው የግብር ግዴታውን በወቅቱ የተወጣ መሆኑን
የሚያረጋግጥ ከገቢዎች ባለሥልጣን የተሰጠ የግብር
ምዝገባ/ክፍያ ምሥክር ወረቀት (Tax Clearance) ወይም
አቅራቢው ከግብር ነጻ የመሆን መብት ካለው ይህንኑ የሚያረጋግጥ
ሰነድ።
የንግድ ስም ምዝገባ ሰነዶች (አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ)።
የቫት (VAT) ምዝገባ ምሥክር ወረቀት።
አቅራቢው ያገኛቸው የጥራት ምሥክር ወረቀቶች (ለምሳሌ ISO
ወዘተ) እና/ወይም ሌሎች ተመሳሳይ ሰርተፍኬቶች፣ ዕውቅናዎች፣
የሽልማት ምስክርነቶች እና የብቃት ማረጋገጫዎች (ካሉ)።
በኢትዮጵያ ውስጥ ለመሥራትና ለመንቀሳቀስ ከአካባቢው
መንግሥት የተሰጠ ፈቃድ።
አቅራቢው በኢትዮጵያ ውስጥ ወይም ከአገር ውጭ የሚገኝን ሌላ
አካል በመወከል የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያውን የሚያቀርብ ከሆነ
የሽርክና (JV)፣ የጥምረት (Consortium) ወይም የማኅበር
ስምምነት ሰነድ።
|
|
የፋይናንስ አቅም
(Financial Standing)
|
አቅራቢው ኦዲት የተደረገ የፋይናንስ ሪፖርት ማቅረብ አለበት።
(ለሽርክና/ጥምረት/ማኅበር (JV/Consortium/Association) ሁሉም አጋሮች በጋራ ሆነው ይህንን መስፈርት ማሟላት አለባቸው)።
|
4. የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ መስፈርቶች (EOI REQUIREMENTS)
ፍላጎት ያላቸው አቅራቢዎች ከታች በዝርዝር በተቀመጡት መሠረታዊ መስፈርቶች ላይ በመመሥረት ምላሻቸውን ማቅረብ አለባቸው፡
- ለሚመለከታቸው አገልግሎቶች የተዘጋጀ ከሃያ አምስት (25) ገጾች ያልበለጠ የድርጅቱ መገለጫ (Company Profile)።
- አግባብነት ያለው የንግድ ሥራና የንግድ ምዝገባ ፈቃድ።
- አቅራቢው የግብር ግዴታውን በወቅቱ የተወጣ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከገቢዎች ባለሥልጣን የተሰጠ የግብር ምዝገባ/ክፍያ ምሥክር ወረቀት ወይም አቅራቢው ከግብር ነጻ የመሆን መብት ካለው ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ።
- የንግድ ስም ምዝገባ ሰነዶች (አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ)።
- የቫት (VAT) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ምሥክር ወረቀት።
- የውጭ አገር ኩባንያ ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመሥራትና ለመንቀሳቀስ ከአካባቢው መንግሥት የተሰጠ ፈቃድ።
- አቅራቢው በኢትዮጵያ ውስጥ ወይም ከአገር ውጭ የሚገኝን ሌላ አካል በመወከል የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያውን የሚያቀርብ ከሆነ የሽርክና (JV)፣ የጥምረት (Consortium) ወይም የማኅበር ስምምነት ሰነድ።
5. የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያን አስመልክቶ (SUBMISSION OF RESPONSES)
መጫረት የምትሹ የንግድ ድርጅቶች የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያችሁን (EOI) በኤሌክትሮኒክ ቅጂ (Soft copy) በሚከተለው የኢሜይል አድራሻ በመላክ እስከ ህዳር 25 ድረስ መድረሱን ማረጋገጥ ይኖርባችኋል፡
- የኢሜይል አድራሻ፡ bids@safaricom.et
- የአቃፊው ስም እና የኢሜይሉ ርዕስ (Folder Name & Email Subject)፡ “EOI – PROVISION OF TALENT POOL AND RESOURCE AUGMENTATION SERVICES
6. ቀጣይ ደረጃዎች (NEXT STEPS)
የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ ምላሾች ከተቀበሉ በኋላ ሳፋሪኮም የሚከተሉትን ተግባራት ሊያከናውን ይችላል፡
- የቀረቡትን የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያዎች መመርመርና መገምገም።
- የቴክኒክ ግምገማ/የሰነድ ምርመራ ማካሄድ እንዲሁም ብቁ የሆኑ ተወዳዳሪዎችን በማጣራት (Screening) ለቀጣዩ ዙር የሚያልፉ አቅራቢዎችን በቅድሚያ መምረጥ (Prequalification of shortlisted suppliers)።
- ለቀጣይ ውይይት/የፕሮፖዛል መጠየቂያ (RFP) ደረጃዎች የሚታሰቡት ዝቅተኛውን መስፈርት የሚያሟሉ አቅራቢዎች ብቻ ናቸው።
7. ማሳሰቢያ (NOTE)
- የሚታሰቡት ዝቅተኛውን መስፈርት የሚያሟሉ አቅራቢዎች ብቻ ናቸው።
- በዚህ የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ (EOI) ደረጃ ምንም ዓይነት የዋጋ ዝርዝር መቅረብ የለበትም።
- የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ ማቅረብ ሳፋሪኮምን ወደ ምንም ዓይነት የውል ስምምነት አያስገባውም። ውሎች የሚፈጸሙት በውድድር ላይ የተመሠረተ የጨረታ ሂደት ከተካሄደ በኋላ ብቻ ነው።
- ሳፋሪኮም ቴሌኮምኒኬሽንስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ኩ በራሱ ውሳኔ የቀረቡለትን ማናቸውንም ወይም ሁሉንም ማመልከቻዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመቀበል ወይም ውድቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው። የሚሰጡ ውሳኔዎች የመጨረሻ ሲሆኑ፣ ውጤቱን ከማሳወቅ ባለፈ ምንም ዓይነት ተጨማሪ ልውውጥ አይደረግም።
- የምላሽ ሰነድ መድረሱ ብቻ ሳፋሪኮምን ከዕጩ ተጫራቹ ጋር ወደ ምንም ዓይነት የውል ስምምነት አያስገባውም። እንዲህ ያሉ ስምምነቶች ተግባራዊ የሚሆኑት ከጨረታ ሂደት በኋላ አሸናፊ ለሆነው ተጫራች የሥራ ሽልማት (Award) ሲሰጥ ብቻ ነው።
- ለዚህ የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ ምላሽ ዝግጅትና አቀራረብ የሚወጣውን ማናቸውንም ወጪ ተወዳዳሪው ራሱ ይሸፍናል።