የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 9ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ማራዘሚያ እንዲሁም 3 የቦታ ኮዶች ከጨረታ የተሰረዙ መሆናቸውን ያሳውቃል – test3.diretenders.com

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 9ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ማራዘሚያ እንዲሁም 3 የቦታ ኮዶች ከጨረታ የተሰረዙ መሆናቸውን ያሳውቃል


Addis Lessan (Nov 21, 2026)

ማስታወቂያ
9ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ተራዝሟል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለ9ኛዉ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በየካ፣ ኮልፌ ቀራንዮ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ አዲስ ከተማ፣ ለሚ ኩራ፣ ጉለሌ፣ አራዳ እና ቦሌ ክ/ከተሞች የሚገኙና ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ጥቅምት 28/2019 ዓ.ም በአዲስ ልሣን ጋዜጣ ባሳወቀው መሰረት የጨረታ ሰነድ ሽያጭ በኦንላይን እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል።

ይሁን እንጅ የጨረታ ሰነድ ሽያጩን ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከህዳር 14/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 18/2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ ሽያጩ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች ኦርጅናል ሲፒኦ ብቻ በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የቦታ ኮዱን እና የጨረታ ቁጥር በመጻፋ ለም ሆቴል በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ህዳር 18/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እሰከ 11፡30 ሰዓት በአካል በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ጊዜያዊ ውጤት ህዳር 24 ቀን 2019 ዓ.ም ለጨረታ በተዘጋጀው ድህረ ገፅ ላይ በቦሌ ክ/ከተማ አዳራሽ በሚደረገው ስነ-ስርዓት ይፋ የሚደረግ ሲሆን ከዚህ በታች የተገለጹ የቦታ ኮዶች ከጨረታ የተሰረዙ መሆናቸውን እናሳውቃለን።

ተ.ቁ

የጨረታ ቁጥር

የቦታ ኮድ

ክ/ከተማ

ወረዳ

1

ጉ/ክ/ከ/04/09

LPP-GU01000280

ጉለሌ

01

2

አ/ክ/ከ/01/09

LPP-AR05000272

አራዳ

05

3

አ/ክ/ከ/02/09

LPP-AR06000277

አራዳ

06

  • የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ጥቅምት 28 ቀን 2019 ዓ.ም በወጣው አዲስ ልሣን ጋዜጣ ላይ መመልከት ይቻላል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ የማህበራዊ የትስስር ገጾችን መመልከት ይቻላል።

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

ከዚህ በፊት የወጣውን ጨረታ ለመመልከት እባክዎን ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ 

https://tender.2merkato.com/tenders/6aeec63e0a538a8082000001 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *