የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች /Building Materials/ በአካባቢ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች /Building Materials/ በአካባቢ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Melekite Dire (Nov 18, 2026)

የአካባቢ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች /Building Materials/በአካባቢ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  • የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድና የአቅራቢዎች መታወቂያ ያላቸው፡፡
  • ሻት የተመዘገቡ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ ቲን ቁጥር ያለው፡፡
  • ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ቢሮ የስራው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ቅድሚያ ይሰጠዋል።
  • የጨረታው ዶክመንት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመከፈል ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ከግዥ ፋይናንስ ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር ዐ8 በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  • የጨረታ ሰነድ በውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ቢሮ ቁጥር 05 ከ1፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓትና ቀን መግዛትና ማስገባት ይቻላል።
  • ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  • ተጫራቾች ብር 50,000.00 / ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ወይም CPO ከዋናው ሰነድ ጋር ማስያዝ አለባቸው፡፡
  • የጨረታው ዶክመንት በታሸገ ፖስታ የእያንዳንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት
  • በተጨማሪ በጨረታ ዶክመንቱ ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው መቅረብ አለባቸው፡፡
  • ያሸነፈው ተጫራች የተጠየቀውን እቃ የጣዥ ትዕዛዝ እንደተሰጠው በእስፔስፊኬሽኑ እና በናሙናው መሠረት በ30 ቀናት ውስጥ በድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን በሚገኝበት መጋዘን አቅርቦ ማስረከብ አለበት፡፡
  • በዶክመንቱ ከተሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈው ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና CPO ወይም በሁኔታ ያልተገደበ የባንክ ጋራንቲ ማሰያዝ መስጠት የሚችል።
  • በጨረታው ሂደት ጨረታውን ለማዛባት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆንና በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
  • ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ዶከመንት ተቀባይነት የለውም።
  • ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ቀበሌ 03 ድሬዳዋ ስልክ ቁጥር 025 112 48 92 ፓ.ሳ.ቁ  446


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *