ወላይታ ልማት ማህበር እ.ኤ.አ የ2026 በጀት ዓመት የማህበሩን ሂሳብ ኦዲት ለማስደረግ ባለሙያዎችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ በውል ለማሠራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 22, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ወልማ  04/2026

ወላይታ ልማት ማህበር እ.ኤ.አ የ2026 በጀት ዓመት የማህበሩን ሂሳብ ኦዲት ለማስደረግ ባለሙያዎችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ በውል ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሠዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች አሟልተው ማቅረብ ያለባቸው መስፈርቶችና ግዴታዎች:-

  1. ለኦዲት ሥራ ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ /AABE/ የተሰጠ የሙያ ፈቃድ ማቅረብ
  2. ከሚመለከተው ሕጋዊ አካል የተሰጠ የሙያ ፈቃድ ማቅረብ፣
  3. ተጫራቾቹ ሙያ ዘርፉ የታደሰ ንግድ /የሙያ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የንግድ የሙያ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ፣
  4. ተጫራቾች በሥራ ላይ የሚያሳትፋቸውን ባለሙያዎች ብዛት የትም ደረጃ፤ የሥራ ልምድ፤ ከእያንዳንዱ ባለሙያ ጋር የተፈፀመውን የቅጥር ውል ኮፒ ወዘተ ማቅረብ፣
  5. ተጫራቾች ስለ መልካም ሥራ አፈፃፀማቸው ከአሁን በፊት የሒሳብ ምርምራ ካደረጉባቸው ድርጅቶች የተሰጣቸውን የድጋፍ ምስክር ወረቀት ማቅረብ፣
  6. ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋው 2 % (ሁለት ፐርሰንት) በባንክ የተመሰከረለት ሲ.ፒኦ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አያይዞ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ፤
  7. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በመከፈል የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ በተከታታይ ባሉት አሥራ አምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በማህበሩ ሥራ ሰዓት ከወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት እና በወላይታ ልማት ማህበር አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች በጥራትና በዋጋ ላይ የተመሠረተ መረጣ መርህ በመከተል የቴክኒክና የፋይናንስ የወዳደሪያ ሐሳቦችን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለብቻ ስምና አድራሻውን በፖስታ በኤንቨሎፕ ላይ በትክክል በመጻፍና ማህተም በማድረግ አሽገው በወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ከፍል ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት እስከ 15ኛው የሥራ ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. የጨረታ ሣጥን በ15ኛው ሥራ ቀን ልክ በ8፡30 ሰዓት ታሽጎ (ተዘግቶ) ፈቃደኛ የሆነ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮችና ታዛቢዎች በተገኙበት ልክ ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት በወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል በይፋ ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው ሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
  10. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት የጠቅላላ ዋጋው 10% አሥር ፕርስንት የውል ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሠከረ ሲ.ፒ.ኦ በማቅረብ ውል መፈረም አለበት፡፡ ለማስያዝ ፈቃደኛ ካልሆነ ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለማህበሩ ውርስ ይደረጋል።
  11. አሽናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተግለፀበት ቀን በኋላ በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልገባ የጨረታ ዋስትናውን ያስቀጣል፡፡
  12. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ እና አሽናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ አላቀርብም ማለት የጨረታ ማስከበሪያውን ያስቀጣል።
  13. አንድ ተጫራች የሚያሠራው ሲፒኦ በሕጋዊ ባለመብት ወይም ድርጅት ስም መሆን አለበት።
  14. የጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም ግልፅ ሆኖ ካልታየ ተቀባይነት አይኖረውም ወይም ከውድድር ውጭ ሊያስደርግ ይችላል።
  15. ልማት ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 09 16 83 34 99 እና 09 13 25 57 29  መጠቀም  ይችላሉ፡፡

ወላይታ ልማት  ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *