Addis Zemen (Nov 22, 2026)
የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ቁጥር 009/2019
ዳሞታ የወላይታ ገ/ሁ/ህ ሥራ ዩኒየን በደቡብ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግሰት በወላይታ ዞን ለሚገኙ አርሶ አደሮች በያዘናው ምርት ዘመን 2019 ከወላይታ ሶዶ ከተማ እና ከሱራ ኮዮ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለማራገፊያ ጣቢያዎች ለበልግ፣መኸርና መስኖ የአፈር ማዳበሪያ ዳፕ እና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
ሰለሆነም ተጫራቾች ከድርጅቱ የማረገፊያ ጣቢያዎችን ዝርዝር መግለጫ መሠረት ለማጓጓዝ የሚፈልገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፋልት መንገድ በአማካይ በኩንታል በአንድ ኪሎ ሜትር ተሰልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንድወዳደሩ ይጋብዛል።
በዚሁ መሰረት
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑ ግብር ከፍሎ የንግድ ፍቃዱን ያሳደሰ እንድሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ያላት፤
- ከሚመለከተው ፍቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ፤
- ከዚህ ቀድሞ በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ስራውን በሚገባ ሰለመወጣቱ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል፤
- የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ ወረዳ ወይም ማራገፊያ ጣቢያ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችሉም፤
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ስፒኦ /CPO/ ብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታ አሸናፊ የሚሆን ማንኛውም ድርጅት ውል ከመፈጸሙ በፊት ያሸነፈበትን ጭነት ማጓጓዣ ዋጋ 10 ፐርሰንት ለውል ማስከበሪያ በቅድሚያ ያስይዛል፤
- ተጫራቾች የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር ቢያንስ 2,400 /ሁለት ሺህ አራት መቶ ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪኖችን የሠለዳ ቁጥር የመኪና ዓይነት እና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዘጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር/1000 /አንድ ሽህ ብር በመክፈል ከዳሞታ የወላይታ ገ/ህ/ሥራ ዩኒየን ዋና ጽ/ቤት ዘውትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላል፤
- የጨረታውን ሰነድ በኢንቨሎፕ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 /ሃያ አንድ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላል።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ21ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየኑ ዋና ጽ/ቤት ይከፈታል። ነገር ግን 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ አሽናፍ የሆነ ድርጅት በመስፈርቱ መሠረት ማሸነፉ ስረጋገጥ በዩኒዬን ማስታወቂያ ቦርድ የሚገለፅ ይሆናል።
» አድራሻ ወላይታ ሶዶ መናሐሪያ ፊት ለፊት ወደ ኦቶና በሚወስደው አስፋልት ላይ ሙሐባና ቻይና ጋራጅ ጎን ይገኛል።
ስልክ ቁጥር 0465510642//0975064075/0913832626/0910432549
ፋክስ 0465522955
ዳሞታ የወላይታ ገበሬዎች ሁለገብ ህብረት ስራዩኒየን
ወ/ሶዶ