በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎ/ዞን የደጀን ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በደጀን ወረዳ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 24, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2019

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎ/ዞን የደጀን ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በደጀን ወረዳ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ እቃዎች ጽህፈት መሳሪያ የተዘጋጁ ልብሶች ብትንጨርቅ፤ የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ ጫማዎች ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች የጽዳት እቃ አሸዋ የውጭ ፈርኒቸር የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1.  በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር ያለውና ማቅረብ የሚችል፣
  2. የታክስ ክሊራንስ /ግብር ስለመክፈሉ ማረጋገጫ/ ያለውና ማቅረብ የሚችል፤
  3. የግዥው መጠን ከ500000/አምስት መቶ ሽህ/ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  4. ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ፎቶ ኮፒ አያይዘው መቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዳቸው አይነት የጫረታ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 400/አራት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ከደጀን ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የተጠየቁትን እቃዎች በተሰጠው ዝርዝር መግለጫ መሠረት ብቻ መሙላት ያለባቸው ሲሆን ከቀረቡት ዝርዝር ውጭ የሞላ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር/ የሞሉትን ጠ/ዋጋ-ግንባታ እቃ ጨረታ 20000 ብር ለአሸዋ ጨረታ 10000ብር ፤ለጽህፈት መሳሪያ ጨረታ 50000ብር ለጽዳት እቃ ጨረታ 10000ብር ለተዘጋጁ ልብሶች ጨረታ 10000ብር ለብትን ጨርቅ ጨረታ 15000ብር ለጫማ ጨረታ 20000ብር ፣ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች 50000ብር ፣ለስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ 50000ብር ለሃገር ውስጥ ፈርኒቸር ጨረታ 5000ብር እና ለውጭ ፈርኒቸር ጨረታ 5000ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ/ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመፈረም እና የድርጅቱን አድራሻ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመፈረም እና ክብ ማህተም በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡30 ድረስ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 4 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቸው ባይገኙም ጨረታውን መ/ቤቱ ይከፈታል።
  9. የጨረታ መክፈቻ ቀን ዝግ/በዓል/ የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  10. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈባቸውን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ሲያቀርብ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል።
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን በሎት የሚያወዳድር ከሆነ በአንድ ምድብ ውስጥ ከተዘረዘሩት እቃዎች ውስጥ ሳይሞሉ መተው አይችልም፡፡ በሎት ያስሞላ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።
  12. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ደ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
  13. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነት በተገለጸባቸው ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ቀርበው ውል መያዝ አለባቸው።
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. የጨረታው ተሳታፊዎች ለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 776 0443 ወይም 058 776 0040 መደወል ይችላሉ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎ/ዞን የደጀን ወረዳ ገ/ጽ/ቤት