Addis Zemen (Nov 24, 2026)
የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 002/2019
የዴኮማ ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒዬን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በቡርጅ ዞን ለሚገኙ አርሶአደርች በያዘነዉ 2019/2020 ምርት ዘመን ሶያማ ከሚገኘው ማዕከላዊ መጋዘኖች ለሰብል አበቃይ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ጣቢያዎች በበልግና በመኸር የአፈር ማዳበሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከድርጅቱ የማረገፊያ ጣቢያዎችን ዝርዝር መግለጫ በመዉሰድ ለመጓጓዝ የሚፈለገዉን የማድረሻ ዋጋ በጠጠር መንገድ በአማካይ በኩንታል በአንድ ኪሎ ሜትር ተሰልተዉ በእያንዳንዱ ጣብያ በመለየት እንድወዳደሩ ይጋብዛል።
በዚሁ መሠረት፡–
- በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለዉ፣ የዘመኑን ግብር ከፍሎ የንግድ ፈቃድ ያሳደስ እንድሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለዉ
- ከሚመለከተዉ ፈቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የስራ ዘርፊ ተሰማርቶ ሥራዉን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ሥራ አፈጻፀም ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ መዋቀር ዉስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይቻልም
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/cpo/ ብር 50,000/ሃምሳ ሺህ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል
- በጨረታ አሸናፊ የሚሆን ማነኛዉም ድርጅት ዉል ከመፈፀሙ በፊት ያሸነፈበትን ጭነት የማጓጓዣ ዋጋ 10% በቅድሚያ ያስዛል።
- ተጫራቾች የተሸከረካርዎችን ዝርዝር ብያንስ 200/ሁለት መቶ/ ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችል መኪና የሰለዳ ቁጥር፤ የመኪና አይነትና የመጫን አቅም የምያስረዳ ፊቃድ ከሰጠዉ መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታዉ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግደታ ይህ የጨረታ ማስታወቅያ በአድስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 1000/አንድ ሺህ/ ከደኮማ ሁለገብ ህብርት ሥራ ዮኒዬን ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታዉን ሰነድ በኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቅያ በአድስ ዘመን ጋዘጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ ማቅረብ ይችላሉ።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከ10ኛዉ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛዉ ቀን በጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸዉ በተገኙበት በዩኒዬን ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ከኛዉ ቀን የሥራ ቀን ካልሆኔ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀዉ ቦታና ሁኔታ ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀኛ።
፡ አድራሻ፡– በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማ አደባባዩ ጋር ከፍ ብሎ
ስልክ፡-0970380799/0972629414/0954796833
ዴኮማ ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒዬን
ቡርጂ– ሶያማ