Be'kur (Nov 23, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ማለትም፡-
- ሎት 01. የጽህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 02. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎቸ፣
- ሎት 03. የምግብ ምርቶች፤
- ሎት 04. የእህል ምርት ውጤቶች፣
- ሎት 05. የቤትና የቢሮ እቃዎች፣
- ሎት 06. የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች፣
- ሎት 07. የጽዳት እቃዎች፣
- ሎት 08. የስፖርት እቃዎችና መገልገያዎች፣
- ሎት 09. ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት እና
- ሎት 10. ጫማና የቆዳ ውጤቶችና ተዛማጅ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡-
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በግብር አመቱ ተገቢውን የታክስና ግብር ግዴታን የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ ታክስ ክሊራንስ፡፡
- የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፤
- የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያለው፡፡
- የጠቅላላ ግዥ መጠን ከብር 500,000(አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የእቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ሎት በቀረበው ብር መጠን ማለትም ሎት 01. ብር 2,500፤ ሎት 02. ብር 1,400፤ ሎት 03. ብር 7,000፤ ሎት 04. ብር 30,000 ፤ሎት 05. ብር 1,000 ሎት 06. ብር 2,000፤ ሎት 07. ብር 3,500፣ ሎት 08. ብር 1,500፤ ሎት 09. ብር 1,500 እና ሎት 10.ብር 1,500 በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ ማህተም በማድረግ፤ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን ናምበር፣ የታክስ ክሊራንስ፣ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ሰነድ የተገዛበት ደረሰኝ ኮፒ በአንድ በታሸገ ፖስታ እና በሌላ ፖስታ የጨረታ ሰነድ ኮፒ በማድረግ በፖስታው ላይ ኮፒና ኦርጅናል ብለው በመጻፍ ት/ቤቱ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር) ከት/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ 1 በመክፍል ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከ14/03/2019 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በአየር ላይ ይቆያል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ማለትም 24/03/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓላት ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ወይም ኮሬክሽን ፍሉድ መጠቀም አይፈቀድም፡፡
- ት/ቤቱ በሚቀርቡ እቃዎች ላይ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ሲሆን እቃዉን በራሱ የትራንስፖርት ወጭ እና የጫኝ አውራጅን ወጭ ታሳቢ በማድረግ መወዳደር ሲሆን በወቅቱ ሀዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡
- ት/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 መሰረት ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል፡፡
- አድራሻ፡- ደ/ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግቢ ስልክ ቁጥር 0920504380፣ 0920506887 እና 0937372810 ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት