የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ለራሱ ለፕላንና ልማት ቢሮ እንዲሁም በፑል አገልግሎት ለሚሰጠው የአብክመ ጣና ሴክሬታሪያት የ2019 በጀት ዓመት የሚውል የተለያዩ ግዥዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 23, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ለራሱ ለፕላንና ልማት ቢሮ እንዲሁም በፑል አገልግሎት ለሚሰጠው የአብክመ ጣና ሴክሬታሪያት የ2019 በጀት ዓመት የሚውል የተለያዩ ግዥዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች፣
  • ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች፣
  • ሎት 4. የፈርኒቸር ዕቃዎች፣
  • ሎት 5. የተሽከርካሪ ጎማ፣
  • ሎት 6. የተሽከርካሪ ጌጣጌጥ፣
  • ሎት 7. ብስክሌት እና
  • ሎት 8. የደንብ ልብስ አቅርቦት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1.  በዘርፉ አግባብ ያለው እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. በታክስ ባለስልጣን የተሰጠ ወቅታዊ የታክስ ክፍያ የከፈለ መሆኑን የሚገልጽ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የግዥው መጠኑ ከብር 500.000(አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ለሚገዙ ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ ብር) በመክፈል በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 310 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
    • ለሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች ብር 30,000፣
    •  ለሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች ብር 22,000፣
    • ለሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ብር 65,000፣
    • ለሎት 4. የፈርኒቸር ዕቃዎች ብር 20,000፣
    •  ለሎት 5. የተሽከርካሪ ጎማ ብር 80,000፣
    • ለሎት 6. የተሽከርካሪ ጌጣጌጥ ብር 19,000፣
    • ለሎት 7. ብስክሌት ብር 12,600 እና
    •  ለሎት 8. የደንብ ልብስ ብር 7,600 በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ስም ቢያንስ ለ73 ቀናት የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በማሰራት ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን የእያንዳንዱን ተቋም በመለየት ለሎት3 (የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች) ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል መመዘኛ እና የዋጋ መወዳደሪያ በማለት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም ከሎት 3 (የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች) ውጭ ያሉትን ዋናውን ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን ብቻ የዋጋ መወዳደሪያ የሚል ፅሁፍ በመፃፍ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 24/2019 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ኘላንና ልማት ቢሮ መሰብሰቢያ አዳራሽ ህዳር 24/2019 ዓ.ም 4፡00 ይታሸግና በዚሁ ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡
  11. አሸናፊው ድርጅት የሚመረጠው ለሎት 3. (ለኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች) እና ለሎት 5. (የተሽከርካሪ ጎማ) በነጠላ ዋጋ፣ ለሎት 8. (የደንብ ልብስ) በንዑስ ሎት ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ሲሆን ለሌሎች ሎቶች በጠቅላላ ዋጋ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ሞልቶ ያቀረበው ድርጅት አሸናፊ ሆኖ የሚመረጥ ይሆናል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ኘላንና ልማት ቢሮ ቁጥር 001 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 64 27 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ