2merkato.com (Nov 25, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ድንጋስ ትሬዲንግ አ.ማ የ2018 በጀትዓመት የውጭ ኦዲት አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ዝርዝር መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል።
|
ተ.ቁ |
የግዥው አይነት |
የጨረታ መለያ ቁጥር |
ምድብ/ ሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር መጠን |
ጨረታው የሚዘጋበት የምከፈትበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
የ2018 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲት አገልግሎት ግዥ |
DTS/Bid01/2019 |
01/2019 |
10,000
|
በ 2merkato.com ከወጣበት ቀን አንስቶ በተከታታይ የሚቆጠር 5 የስራ ቀን ሆኖ በ6ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4:30 ላይ ይከፈታል። |
በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
2. በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርቡ።
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ድንጋስ ትሬዲንግ አ.ማ ስም CPO ወይም በባንክ ዋስትና የተረጋገጠ ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት።
5. ከላይ የተገለጸውን መስፈርት አሟልተው በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በ ስ.ቁ 0946474805 በመደወል የ ጫረታውን ሰነድ መግዛት።
6. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ከቴክኒክ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር አያይዘው በቴክኒክ ኢንቨሎፕ ውስጥ ማቅረብ አለባቸው።
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቴክኒካል ዋናና ኮፒ እና የፋይናንሻል ማስረጃዎችን ዋናና ኮፒ በመለየት ዋና እና ኮፒ በአንድ ፖስታ ካኪ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዥ ከተጠቀሰው የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በአስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
አድራሻ፡– የድርጅቱ ቅ/ጽ/ቤት ሸገር ሲቲ፤ ገ/ጉጀም ክ/ከተማ ኬላ ኦልብራይት አካዳሚ።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር +251946474805 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ድንጋስ ትሬዲንግ አ.ማ