Addis Zemen (Nov 26, 2026)
የድርድር ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ አቶ ሱማሞ ዶባሞ ኢርግቾ በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሰረት የኪራይ ክፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የዳቦ ማምረቻ ማሽነሪ ባሉበት ሁኔታ በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተከራዩ ስም |
የሚሸጠው ንብረት ዓይነት እና ዝርዝር መረጃ |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የድርድር ጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር) |
የድርድር ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ |
የድርድር ጨረታ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
የጨረታ ሁኔታ |
|
1 |
አቶ ሱማሞ ዶባሞ ኢርግቾ |
1. Rotary Oven 16 Try (01) set 2.Volumetric Dough Divider የሊጥ ማከፋፈያ (01) set. 3. Mixer የሊጥ መቀላቀያ (01) set 4. Molding machine የሊጥ ቅርጽ ማውጫ (01) set 5. Brade slicer የዳቦ መቁረጫ አንድ (1) set 6. French tray and rottey for ATDF 250 ሁለት (02) set 7. Flat tray with Trolley for ATDF 250 ሁለት (02) 8. Diesel Generator አንድ (01) set ናቸው። |
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን፣ ሆሳዕና ከተማ አስ/ር፤ በአራዳ ቀበሌ ክልል ውስጥ በተቋቋመው በአቶ ሱማሞ ዶባሞ (በተከራይ) የዳቦ ማምረቻ ቦታ፤ |
9,792,010.52 |
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሀዲያ ዞን፣ ሆሳዕና ከተማ አስ/ር፤ በአራዳ ቀበሌ ክልል ውስጥ በተቋቋመው በአቶ ሱማሞ ዶባሞ (የተከራይ) የዳቦ ማምረቻ ቦታ፤ |
ታህሳስ 14 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 እስከ 6፡00 |
ድርድር ጨረታ |
የድርድር ጨረታው መመሪያ
1. በድርድር ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስምና አድራሻ በመጥቀስ፤ የታደሰ መታወቂያ ኮፒ፤ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ ወይም 20% በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ ገዢው የሚገዛበትን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት እስከ ታህሳስ 13 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል።
2. ንብረቱ የሚገኘው ሆሳዕና ከተማ አስ/ር፤ በአራዳ ቀበሌ ውስጥ በተከራይ ማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው። ተደራዳሪ ተጫራች አሸናፊ ከሆነ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) መክፈል ግዴታ አለበት። በተያያዘ ንብረቶችን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነጻ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል። አሸናፊ ተጫራች ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት/ በሕግ የተወሰነ ታክስ ጨምሮ የሚጠየቁ ማንኛውንም ክፍያ በቅድሚያ በመከፈል ንብረቱን ይረከባል።
3. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ/በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተደራዳሪ ተጫራች ንብረቱን ይረከባል።በድርድር ጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ ሁሉ በድርድር ጨረታ መሳተፍ ይችላል፤
4. ንብረቱን በከፊል ለመከራየት የሚፈልግ ተጫራች ከሆነ ቢያንስ ያሸነፈበትን ዋጋ 20% ቅድሚያ በመክፈልና የባንኩን የሊዝ ኪራይ መስፈርት በማሟላት በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ የማሽነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል። ሆኖም ግን በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የድርድር ተጫራች አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።ለተሸነፉ ተደራዳሪ ተጫራቾች በጨረታው ያስያዙት የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
5. ንብረቱ በባንኩ የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተደራዳሪ ተጫራች የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀክቱ ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ–ሁኔታዎች መስማማት ይጠበቅበታል። በተጨማሪም የድርድር ጨረታ አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን ለማስተዳደር የሚወጡ ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ ይጠበቅበታል።
6. የድርድር ጨረታ አሸናፊ የካፒታል ዕቃው ካለበት ቦታ ወደ ሚፈለግበት ቦታ ማጓጓዣ ወጪ፤የጉዞ ኢንሹራንስ፤ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው ይከፍላል።
7. የድርድር ጨረታው ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኘበት ታህሳስ 14 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በኢትዮጰያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ሎን ወርክአውት ዲቪዥን ቢሮ ይደረጋል። ስለ ንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጰያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-180-1528/38 ደውሎ ማነጋገር ይችላል። ንብረቶቹን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከድርድር ጨረታ ቀን በፊት ባሉት ጊዜያት ቀጠሮ በመያዝ ንብረቶቹ በሚገኙበት በተከራይ ማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይቻላል። ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የድርድር ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። በተጨማሪም ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት