Addis Zemen (Jun 06, 2026)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለመምሪያዎች እና ለጽ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ለ1ኛ ዙር በሎት ጠቅላላ ድምር
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት 2 ኮምፒተርና ተዛማጅ እቃዎች
- ሎት 3 የጽዳት እቃ
- ሎት 4 የመኪና ጎማ
- ሎት 5.ሞተር ብስክሌት ጥገና
- 6 የመኪና ዲኮር
- ሎት 7. የስፖርት ትጥቅ
- ሎት 8. የውጭ ፈርኒቸር
- 9. የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር
- 10 የኮምፒተር ተዛማጅ ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾቾ መወዳደር ይችላሉ።
1 በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያለውና ማቅረብ የሚችል
2. የግዥው መጠን ከብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቁሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አየይዘው ማቅረብ አለባቸው።
4 የሚገዙትን ዕቃ አይነትና ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህትም ማድረግ አለባቸው።
6. ተጫራቾች ሳምፕል ላልቀረበባቸው የግዥ ሎት በተጠየቀው ዝርዝር መሰረት ያሸነፈው ድርጅት ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባችዋል ሆኖም ያቀረቡት ሳምፐል ውል ይዘው ዕቃው ገቢ ከተደረገላቸው በኋላ ይመለስላችዋል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር/100/መቶ ብር/ በመክፍል የደ/ማ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ድሮው ንግድ ባንክ ማግኘት ይቻላሉ።
8. የኮምፒተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ጥገና በደ/ማ/ከ/አስ/ መምሪያዎች ቢሮ ድረስ በመምጣት መጠገን የሚችል እና የሞተር ብስክሌት ጥገና ደበረማርቆስ ከተማ ጋራዥ መኖር ያለው መሆን አለበት።
9. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ/c.p.o/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመስረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በደ/ማ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ስም በተዘጋጀ መሂ-1 ደረሰኝ 1% በመቁረጥ ማቅረብ ይኖርባችዋል።
10. ማነኛዉም ተጫራች ሰነዱን ሞልቶ በታሸገ ፖስታ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳድር የስራ ሂደት የቀድሞው ዋናው ንግድ ባንክ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ በአየር ላይውላል።
11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የደ/ማ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቅጥር ግቢ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዚሁ እለት በ4፡30 ሠዓት ይከፈታል የጨረታ መክፈቻዉ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
12. አሸናፊው ድርጅት የደ/ማ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ን/ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ይዞ በመምጣት ማስረከብ አለበት።
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 0587713362 መምሪያው
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ