በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሞባይሎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ ጊርቦክስ እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሞባይሎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ ጊርቦክስ እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 06, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 90/2018 91/2018 92/2018 93/2018

94/2018 95/2018 96/2018 97/2018 እና 98/2018

በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ //ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሞባይሎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ ጊርቦክስ እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 90/2018 በቀን 01/10/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 91/2018 በቀን 4/10/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 92/2018 በቀን 8/10/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 93/2018 በቀን 11/10/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 94/2018 በቀን 15/10/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 95/2018 በቀን 18/10/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 96/2018 በቀን 22/10/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 97/2018 በቀን 25/10/2018 . እና ጨረታ ቁጥር 98/2018 በቀን 29/10/2018 . በመሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን በማሟላት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

በመሆኑም

1. በቅ//ቤቱ ለሚካሄደው ጨረታ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የተከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ 200-600 ከሰዓት በኋላ 700-1100 እንዲሁም ቅዳሜ ጥዋት 200-600 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ //ቤት ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን ቅጥር ግቢ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል።

3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ካርጎ መጋዘን እና ገርጂ መጋዘን እስከ ግንቦት 01/2018 /ም፤ ግንቦት 4/2018 .ም፣ ግንቦት 8/2018 .ም፣ ግንቦት 11/2018 .ም፣ ግንቦት 15/2018 /ም፣ ግንቦት 18/2017 / ግንቦት 22/2018 .ም፣ ግንቦት 25/2018 .ም፣ ግንቦት 29/2018 . ከቀኑ 800 ተዘግቶ በዚያው ቀን 815 የሚከፈት ይሆናል።

5. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ቅጾች መሠረት ለመረጡት ዕቃዎች ኮድ የተሰጠ ዋጋ፣ የተጫራቾች ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማና የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ(CPO) እና ከላይ በተ. 1 የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ በመፈረም አዲስ አበባ ኤርፖርት ///ቤት ገርጂ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን መግዣ ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም።

7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

8. የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ 05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለባቸው።

9. ከላይ በተ/ 8 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት .. (CPO) ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

  • በተራ ቁጥር 01 – 09 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 90/2018 በቀን 01/10/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 91/2018 በቀን 4/10/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 92/2018 በቀን 8/10/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 93/2018 በቀን 11/10/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 94/2018 በቀን 15/10/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 95/2018 በቀን 18/10/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 96/2018 በቀን 22/10/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 97/2018 በቀን 25/10/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 98/2018 በቀን 29/10/2018 . ከጠዋቱ 400 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የምናካሄድ መሆኑን እያሳወቅን፣ የዕቃዎችን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ //ቤት ገርጂ እና ካርጎ ዉርስ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል።

10. በሃራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00/አንድ መቶ ሺህ/ ለየዘርፉ CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣

11. ለጨረታ የቀረቡት የዕቃዎች ዋጋ ከቫት በፊት የተሰጠ መሆኑ እናሳውቃለን።

12. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች በተናጠል ሳይሆን ለጨረታው ሰነዱ በተሰጠ ኮድ ቁጥር ብቻ የሚሸጥ መሆኑን እናሳውቃለን።

13. //ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው!

14. በቅ//ቤት ደረጃ እየተካሄደ ያለውን የጨረታ አድማስ ለማስፋት፣ ፈጣን የዕቃዎች ማስወገድ ሥራ በማከናወን እና ገቢን በወቅቱ ለመሰብሰብ እንዲቻል ጨረታዎችን በወረቀት አልባ (Online) አሠራር ለማስኬድ ከኦክሽን ኢትዮጵያ ኢማ ጋር ለመሥራት በመታሰቡ ዘወትር ሐሙስ የሚካሄደውን ግልፅ ጨረታ በቀጥታ ሙሉ በሙሉ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኢማ በወረቀት አልባ (Online) የሚካሄድ መሆኑን እናሳውቃለን፤

15. የኦክሽን ኢትዮጵያ . መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር +251 90 511 5511 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፤

ለተጨማሪ መረጃ ቦሌ ኤርፖርት በስልክ ቁጥር 011 668 4537 እና 011 668 4193 ደዉሎ ይጠይቁ።

የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ //ቤት