የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ንብረቶች በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ንብረቶች በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 28, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በእዋጅ ቁጥር 97/90 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘረውን ንብረት በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የቀድሞ ተበዳሪው/ የመያዣ ሰጪው ስም

የንብረቶች ዓይነት በጥቅል

የማሽነሪ ስም

የጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር)

ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ

የጨረታ

ሁኔታ

ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

1

ኤምቱኬ ኢንጅነሪንግ /የተ/የግ/

ማሽነሪዎች እና እኩፕመንት

የእንጨት ሥራ ማሽነሪ (Surface planner m/c, Circular saw m/c,Edge bending m/c,Copy lathe m/c, Combined surface or thickness planner m/c etc)

ብር 6,185,295.80 ( ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና አምስት ብር ከሰማንያ ሳንቲም)

 

ገላን ከተማ ኤም

ቱኬ ኢንጅነሪንግ

ፋብሪካ ቅጥር

ግቢ ውስጥ

 

ድርድር

ሐምሌ 30 ቀን 2018 . ከጠዋቱ

4:00-6:00 ሰዓት

 

2

የብረት ሥራ ማሽነሪ (lathe m/c,universal milling m/c,press brake m/c, scroll bending m/c,hydraulic bending m/c, motor unit,tube drilling m/c etc)

ብር 26,174,64444 (ሃያ ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አራት ብር ከአርባ

አራት ሳንቲም)

3

ዎርክ ሾፒ ዩትልትስ(Air compressor ,hand pallet,  liquid thank)

ብር 523,134 (አምስት መቶ ሃያ ሦስት

ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ አራት ብር)

4

ስቶን ዎርክ ማሽን (Special shaped stone polishing, multi-blade bridge block cutter m/c,stone surface thickness calibrating m/c etc)

ብር 1,701,600.00 ( አንድ ሚሊዮን

ሰባት መቶ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ብር)

 

5

የቢሮ ዕቃዎች

ብር 650,051 (ስድስት መቶ ሃምሳ ሺህ ሃምሳ አንድ ብር)

6

ጀነሬተር

ብር 697,151 (ስድስት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ አንድ ብር)

7

ካርጎ ትራክ

3-01-77197 AA

ብር 410,562.00 (አራት መቶ አስር ሺህ አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ብር)

ማሳሰቢያ፤

  1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና /ቤት ሁለተኛ ታወር ምድርቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 350 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ሐምሌ 30 ቀን 2018 . 400 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፤
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /../ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
  3. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ 15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው /ቤት ታወር ሁለት 5 ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው አካላትን ወክሎ በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ/ መተዳደሪያ ደንብ ከእነ ማሻሻያዎቹ (ካለ) የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፍቃድ፣ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፡፡
  6.  አንዳንድ ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም የሚፈለገውን ቀረጥ/ታክስ ለመንግስት ለመክፈል ይገደዳል፡፡
  7.  ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ይሆናል፡፡
  8. የንብረቱ ስመንብረት ለገዥው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል:: ገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈፅማል፡፡
  9.  የጨረታ አሸናፊው ማሽነሪዎችን ለመንቀልና ለማጓጓዝ የሚያስፈልግ ወጪ በራሱ ይሸፍናል፡፡
  10. ንብረቶቹ ለጨረታ የቀረቡት በየተራ ቁጥሩ በተናጠል ነው፡፡
  11.  በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና /ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክትስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524-53-73/ 011-524-42-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።
  12. ተጫራቾች አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ንብረቶቹን መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  13. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ልማት ባንክ