ዘመን ባንክ አ.ማ. ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን (የቢሮ ፈርኒቸሮችን) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ዘመን ባንክ አ.ማ. ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን (የቢሮ ፈርኒቸሮችን) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


2merkato.com (Jul 11, 2026)

ዘመን ባንክ አ.ማ. ያገለገሉ ንብረቶች እና ሌሎች ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

(በድጋሜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ)

ዘመን ባንክ አ.ማ. ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን (የቢሮ ፈርኒቸሮችን) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

የጨረታ ደንቦች

1.  ንብረቶችን ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾት ከሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት  ጎፋ መብራት ኃይል ስኩል ኦፍ ቱሞሮ ት/ቤት አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ መመልከት ይችላሉ ወይም በስልክ ቁጥር 0115 57 58 25/ 011 668 78 09 በመደወል ወይም ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው በባንኩ ዋናው መስሪያ ቤት 12ኛ ፎቅ ላይ በንብረት እና ሎጂስቲክ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።

2. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና የዋጋ መሙያ ቅጽ ከባንኩ የንብረት አስተዳደርና ሎጂስቲክስ መምሪያ በመግዛትና እና በመሙላት በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች በምድብ (ሎት) ተለይተዉ ከተቀመጡት ንብረቶች የመረጡትን ለመግዛት የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ህንጻ 12ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

4. ጨረታው ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ላይ በባንኩ ህንጻ 19ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

5. ጨረታው በሚካሄድበት ዕለትና ሰዓት መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው።

6. አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ለባንኩ ክፍያ መፈጸም አለበት።  ይህን ባያደርግ ግን ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።

7. ንብረቶቹን ከማስተካከል፣ ከመጫንና ከማጓጓዝ ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ክፍያ ገዢው ይከፍላል።

8. ተጨማሪ የጨረታ ደንቦች የጨረታ ሰነድና የዋጋ መሙያው ቅጽ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

9. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በመሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ዘመን ባንክ አ.ማ.


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *