Addis Zemen (Jul 19, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው መስተዳድር ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ፡–
- የፅህፈት መሳሪያዎች
- የፅዳት እቃዎች
- የኤሌክትሮንክስ እቃዎች
- ቋሚ የቢሮ እቃዎች
- ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ጎማዎችን
- ባጃጅና ሞተር ሳይክሎችን
- ለኤሌክትሪክና ለውሃ ዝርጋታ የሚያገለግሉ እቃዎች
- ለቴክንክና ሙያ ኮሌጅ ሥልጠና የሚያገለግሉ እቃዎችን
- የደንብ ልብሶችን
በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፡–
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የዘመኑን ግብር ከፍሎ ማጠናቀቁንና፣ ጨረታ ላይ እንድሳተፍ የሚል ማስረጃ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN No.) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ፎቶ ከፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 3000.00( ሦስት ሺህ ብር) በመክፈል ከሞጆ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ CPO ብር 60,000.00(ስልሳ ሺህ ብር) ሲሆን ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ የትኛውንም የዋስትና ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ፎቶኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል።
- ጨረታው የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሞጆ ከተማ ገንዘብ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ውስጥ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
- አሽናፊው ያሸነፈበትን የእቃ አይነት አሸናፊ መሆኑን ካወቀበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ የእቃውን ናሙና ማቅረብ አለበት።
- የጨረታው አሸናፊ እቃዎቹን እስከ ሞጆ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያና በስልክ እንደተገለፀ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ከሞጆ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ጋር መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ገቢ ይሆናል።
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለጸለት ያሸነፈበትን እቃ ብዛት አባዝቶ የጠቅላላውን ዋጋ 10% የውል ዋስትና ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) ለሞጆ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ብሎ በመፃፍ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- መስሪያ ቤቱ ከሚያደርገው የግዢ ውል 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ መገንዘብ አለበት።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡–
ስልክ ቁጥር፡-0221161644/2239 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት