በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና የህትመት ውጤቶችን ለማሳተም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና የህትመት ውጤቶችን ለማሳተም ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 21, 2026)

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር አፋ-01/2019

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የቢሮና የቤት ቋሚ ዕቃዎች፣አላቂ ጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ኤሌክትሮኒክስ እና የመኪና ጎማዎች፣የመኪና መለዋወጫ፣የህንጻ ቁሳቁስ፣ የባህል አልባሳትና የህትመት ውጤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሳተም ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. በዘርፉ የታደሠ ንግድ ፈቃድ

2. ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ስራ ፈቃድ

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት

4. በመንግስት አቅራቢነት የተመዘገበ

5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት ያለው

1. ተጫራቾች በየሎቱ ወይም በሚወዳደሩበት ዕቃዎች 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብለተሸናፊዎች ይመለስላቸዋል።

2. በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከአፋር ብ/ክ/መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 01 የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ።

3. ማንኛውም የጨረታ ተወዳዳሪ የሚያቀርበውን የእቃዎች ዋጋ በግልጽና በማያሻማ መልኩ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ከዚህ መመሪያ ጋር በተያያዘ ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ የነጠላ እና የጠቅላላ ዋጋውን ከነቫቱ ሞልቶ ከላይ የተጠቀሱትና ማስረጃዎች አሟልቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ በመለየት በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ሰመራ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ምድር ላይ በሚገኘው ክፍል ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10ቀናት የሚቆይ እና በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት የሚዘጋ ሆኖ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻው ቀን በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምክንያት በሚከፈትበት ጊዜ ሳገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።

5. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
ሠመራ