የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Aug 23, 2026)

የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ለመሸጥ

የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ 03/2018

የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

.

የታርጋ ቁጥር

የተሽከርካሪ ዓይነት

የሻንሲ ቁጥር

የሞተር ቁጥር

የተመረተበት ዘመን

የሚይዘው የሰው ብዛት

1

. 03-61394

Nissan Pick up

ADNJ980 000E006170

QD32-277413

2009

5

2

. 03-52805

Nissan Minibus

JNITG4E25 ZO-784710

ZD30-209097K

2008

11

3

ኢት 03-51714

Bishoftu Pick up

EBPH4C4B 473001112

4JB1T1-40402839Z

2014

5

4

. 03-86040

Toyota Pick up

AHTFR22 G006062522

2KD-5833102

2012

5

5

ኢት-04-08814

Toyota Pick up

LN106.0087890

3L.3399716

1998

5

6

ኢት 03-10460

Toyota Pick up

YN850055605

2Y-0788336

1993

5

7

ኢት 03-12682

Toyota Pick up

YN85-00555599

2Y-0788240

1998

4

8

ኢት 03-10473

Toyota Automoble

KE706206295

4K-6572619

1986

5

9

ኢት -03-12680

Toyota Minibus

RZH112-0004244

1RZ-0038936

1998

10 ኩንታል

10

ኢት 03-10458

Mitsubishi Pick up

JMYJNK-340WP01568

4D56KC8516

2000

5

11

ኢት 03-15051

Toyota Minibus

0021962

1477886

1998

11

12

ኢት 3-51715

Bishoftu Medibus

EBDHM32 4051000078

20140000403

2014

32

13

ኢት 3-28907

HUNDAYE/Van

KMCGKRA FP6C027483

D4AF-5261563

2005

 

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆነው ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሠነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሃያ ሁለት ማዞሪያ በሚገኘው የድርጅቱ ዋናው /ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሸጫ የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር/ ከፍለው የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

3. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ከነሐሴ 27 ቀን 2018 እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 . ቅዳሜን ጨምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 300 እስከ 1000 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።

4. ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሉ እና የጉምሩክ ቀረጥ ግብር ወጪ ካለው ድርጅታችን የሚሸፍን ሲሆን የስም ማዘዋወሪያ፣ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎች ግን በገዥው ይሸፈናል።

5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የሚገዙት ተሽከርካሪ ብር 100,000.00 / አንድ መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት፣ ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ሲፒኦ/ እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋልየሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።

7. የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋናው /ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ቦታ ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

8. የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀ በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።

9. ድርጅቱ ያወጣውን ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።

10. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሽከርካሪውን 10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።

11. ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት ቦታ ሃያ ሁለት የድርጅቱ ዋና /ቤት ግቢ፣ አያት ደራርቱ አደባባይ በሚገኘው የድርጅቱ ግቢ እና ቦሌ ካርጎ ጎን በሚገኘው የድርጅቱ ግቢ ውስጥ ነው።

12. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር – 09 14 34 13 42 / 09 12 03 33 91 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *