Addis Zemen (Sep 08, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት
- አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣
- የደንብ ልብስ
- የጽዳት እቃዎች
- የመስተንግዶ አገልግሎት
- የትራንስፖርት አገልግሎት፣
- የህትመት አገልግሎት
- ቋሚ እቃ እና
- የድንኳን ኪራይና የዲኮር ስራዎች በመንግስት በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. ሕጋዊ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
2.የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ና በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ እንዲሁም የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ያላቸው።
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ያጠቃለለ ና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በታሸገ ፖስታ በወረዳው ፋይናንስ ግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-11፡30 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ማለትም በየሎቱ
- ሎት 1 16,328 (አስራ ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ስምንት ብር ብቻ)
- ሎት 2 7,216 (ሰባት ሺህ ሁለት መቶ አስራ ስድስት ብር ብቻ)
- ሎት 3 11,300 (አስራ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ብር ብቻ)
- ሎት 4 30,875 (ሰላሳ ሺህ ስምንት መቶ ሰባ አምስት ብር ብቻ)
- ሎት 5 20,665 (ሃያ ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ አምስት ብር ብቻ)
- ሎት 6 10,280 (አስር ሺህ ሁለት መቶ ሰማኒያ ብር ብቻ)
- ሎት 7 8,179 (ስምንት ሺህ አንድ መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር ብቻ)
- ሎት 8 8,300 (ስምንት ሺህ ሶስት መቶ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የእያንዳንዱ የሚወዳደሩበት ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የእቃውን ናሙና ዝርዝር ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸው።
6. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ የኢትዮዽያ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል በወረዳ 08 በፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 24 መውሰድ ይችላሉ።
7. ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 24 ይከፈታል።
8. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን እቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% (ፐርሰንት ) የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጽ/ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈጸም ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን እቃዎች ርክክብ የሚፈጽሙበት በራሳቸው ትራንስፖርት ሆኖ በወረዳው ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ነው።
10. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ መሞከር በህግ ያስጠይቃል።
11. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
12. መ/ቤቱ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ከአንድ በላይ ሎቶች መወዳደር ከፈለጉ የየሎቱን የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የፋይናንስ ጽ/ቤት በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 6-66-16-14 ደውለው ያነጋግሩን።
አድራሻ፡-ፊጋ ሰፈር ከበሻሌ ንግድ ባንክ ወደ ሰሚት በሚወስደው አስፓልት መንገድ ሳፋሪ ት/ቤት ከመድረሶዎት በፊት መሲ ህንጻ ወረድ ብሎ።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት