Addis Zemen (Sep 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በጂማ ዞን የሸቤ ሶንቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡-
- የጽሕፈት መሣሪያና አላቂ ዕቃዎች
- ፈርኒቸር
- ጀኔሬተር
- የደንብ ልብስ
- የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች
- ሞተርሳይክል
- የመኪና ጎማ
ስለዚህ በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ፍቃድ ያሳደሱ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን ኦሪጅናልና ፎቶኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ /VAT እና TIN No ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሰርተፍኬት ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ለእያንዳንዱ የዕቃ ዓይነት ብር 20000 ሕጋዊነቱ ከተረጋገጠ ባንክ በ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ከሸቤ ሶንቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ 200 ብር በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ በ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች አስፈላጊውን ሰነድ በሙሉ ፎቶ ኮፒውን በአንድ ፖስታ ውስጥ ከተው ኦሪጅናሉን ደግሞ በሌላ አንድ ፖስታ ውስጥ ከተው, technical document በአንድ ፖስታ ውስጥ ከተው ባጠቃላይ በ 3 ፖስታዎች ውስጥ ከተው, ፖስታዎቹን በሰም አሽገው ላዩ ላይ ፈርመውና ማሕተም አድርገውበት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 15ኛው የሥራ ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ መከተት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በመሥሪያ ቤታችን የግዥ ከፍል (ቢሮ ቁጥር 3) የሚከፈት ይሆናል።
- የተጫራች ሰነዶች ቀርቦ ተጫራች በአካል ባይገኝም ጨረታው ይከፈታል።
- አሸናፊ ሆኖ የተገኘ ተወዳዳሪ የሚታዘዘውን ዕቃ በሙሉ ወጪውን ችሎ እስከ መሥሪያ ቤታችን ድረስ የሚያቀርብ ይሆናል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሸቤ ሶንቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት