በቦሌ ክ/ከተማ ለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት አመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በቦሌ ክ/ከተማ ለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት አመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 13, 2026)

የመጀመሪያ ዙር የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በቦሌ /ከተማ ለም 2 ደረጃ /ቤት 2019 በጀት አመት በሎት1የደንብ አልባሳትና የስፖርት ትጥቅ ዕቃዎች በሎት2አላቂ የቢሮ ዕቃዎች በሎት3 አላቂ የጽዳትና ሌሎች ዕቃዎች፣ በሎት4አላቂ የትምህርት ዕቃዎች በሎት5የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በሎት6የተለያዩ የህትመት ውጤቶች /በወረቀት እና በባነር አገልግሎት በሎት7ለህክምና ቁሳቁሶችና መድኃኒቶች በሎት8ለቤተሙከራ ቁሳቁሶችና ኬሚካሎች በሎት9 ለቢሮ ውስጥ ፈርኒቸር እና ለተገጣጣሚ ዕቃዎች በሎት10 ለስልጠና የሚሆን የታሸገ ውሃ እና ቆሎ በሎት11የሀገር ውስጥ የትራንስፖርት /የታክሲ/ አገልግሎት፣ በሎት12የካፌ እና የቁርስ አገልግሎት በሎት13የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና በሎት14ለህንጻ እና ለተገጣጣሚ ዕቃዎች ጥገና እንዲሁም የቢሮ መከፋፋል /የፓርትሺን/ ስራ በሎት15የመጸዳጃ ቤትና ሌሎች ፍሳሽ የማስወገድ አገልግሎት፣ በሎት16ለደንብ ልብስ ስፌት፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፣

በዚህም መሰረት በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች፡

1- በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑንግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN number /ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT የተመዘገቡና ለመመዝገባቸውም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል::

2- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ከመ/ቤቱ በወሰዱት የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጉልህ በሚታይ መልኩ ከቫት በፊትና ከቫት በኋላ ያለውን ዋጋ ፅፈው የድርጅቱ ተወካይ ስምና ፊርማ እንዲሁም የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርገው በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

3- ተጫራቾች ለወሰዱትና ለተወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት በሚሞሉት አጠቃላይ ዋጋ ላይ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖባቸዋል::

4- ተጫራቾች ናሙና እንዲገባ በተጠየቀባቸው የዕቃ አይነቶች ሁሉ ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡

5- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በአንድ ሎት ብር 150.00/ ብር አንድ መቶ ሃምሳ/ በመክፈል ከመ/ቤቱ //ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት መግዛትና መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡

6- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ካደራጃቸው /ቤት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ደብዳቤ ቀጥታ ለመ/ቤታችን ደብዳቤ ማጻፍ ይኖርባቸዋል፤ ራሳቸው አምርተው ለገበያ ከሚያቀርቡት ወይም ተጨማሪ እሴት ጨምረው ከሚያቀርቡት ዕቃ ወይም ምርት ውጪ የተዘጋጀ ዕቃዎችን ገዝተው በሚወዳደሩበት ጊዜ እንደማንኛውም ተጫራች ድርጅት የጨረታ ሰነድ መግዛት፣ የጨረታና የውል ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል::

7- ተጫራቾች አሽናፊ ሆነው ለተገኙባቸው እቃዎች የሞሉትን አጠቃላይ ዋጋ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO በማስያዝ ዉል መዋዋል ይኖርባቸዋል፡፡

8- ተጫራቾች ላሸነፉበት ዕቃዎች /ቤቱ ምንም አይነት የዋጋ ለውጥ ሳያደርግ ብዛቱን 20% ዝቅም ከፍም አድርጎ ሊያስተካክል ይችላል፡፡

9- ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ ሰነድ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግና በኤንቨሎፕ በማሸግ ማስታወቂያው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት /ቤቱ በአዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 3 በመገኘት በሰዓቱ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10- የጨረታ ሰነዱን የመመለሻ ቀንና ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም::

11- የጨረታው ሳጥን ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ዕለት አንስቶ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በአስረኛው ቀን 1130 ከት/ቤቱ የግዥ ኮሚቴ አባላትና የሚመለከታቸው ታዛቢ አካላት በተገኙበት ታሽጐ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እና/ወይም ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡

12- ውል የተዋዋሉ አሸናፊዎች የአሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት የግዥ ፈፃሚው /ቤት ንብረት ማከማቻ ክፍል ውስጥ ማምጣትና ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ ለም 2 ደረጃ /ቤት ገርጂ ታክሲ ማዞሪያ አካባቢ ከኮሪያ ሆስፒታል ጎን

ስልክ 0116 394 668 / 0116 295 040

በቦሌ /ከተማ ለም 2 ደረጃ /ቤት