Addis Zemen (Sep 15, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን አራብሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳ ውስጥ ላሉት ለመንግስት መ/ቤቶች ለ2019 ዓ.ም ለአንደኛ ዙር የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል
- የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣
- አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- የጽዳት እቃዎች ሞተር ሳይክል ጎማዎች፣
- የግንባታ እቃዎች፣
- ኤሌክትሮኒክስ፣
- ቋሚ የቢሮ እቃዎች የመኪና ኪራይ የተለያዩ የእትመት ስራዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛቹሀል።
1.በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የ2018 ዓም የከፈሉና የ2019 የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
2.ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ከ5/01/2019 ዓ.ም እስከ/26/1/2019 ዓ.ም ድረስ ለእያንዳንዱ ንግድ ዘርፍ ላይ የማይመለስ ብር 800 (ስምንት መቶ ብር) ከፍለው ከገላን አራብሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
3.ተጫራቾች ላለፉት ዓመታት ማለትም በ2018 ዓ.ም ግዢ ላይ በአቅራቢነት ችግር ያልፈጠሩ ጥሩ የአቅራቢነት ባህሪይ ያላቸው መሆኑን ከፌዴራል ወይም ከክልል ወይም ከከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥ መ/ቤት የምስጋና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።
4.ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ ከጨረታው ሰንድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5.ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት።
6.ተጫራቾች የእቃዎቹን ዋጋ ዝርዝር የተጠየቀውን “Specification ሳይለውጡ የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ላይ ዋጋው ከነ ተጨማሪ እሴት ታክስና VAT በመሙላት ስማቸውን ፊርማችውንና አድራሻቸውን በማስፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንታቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በማድረግ በአንድ ትልቁ ፖስታ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ 26/01/2019 ዓም ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ጨረታው ከመዘጋቱ ከ4፡00 ሰአት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በ26/01/2019 ዓም በ4፡30 ሰአት ይከፈታል። ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይንም ወኪላቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግድውም።
8. የጨረታው ሳጥን ከታሸገ ወይንም –ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
9.የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ከውል ሰጪ መስሪያ ቤት ጋር በሚደረገው የውል ስምምነት መሰረት ገላን አራብሳ ለሚገኘው በውል ሰጪ ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል።
10.መ/ቤታችን በሚያወዳድረው እቃዎች ብዛት ላይ እንደ አስፈላጊነቱ 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል።
11.ተጫራቾች እቃዎቹን አሸንፈው ለማቅረብ ሲዋዋሉ ካሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ከታወቀ ባንክ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።
12.ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊ መሆናቸውን ከተገለጸ ከ 5 ቀን በኋላ በውል ሰጪ መስሪያ ቤት ድረስ በአካል በመገኘት የውል ስምምነት መፈጸም አለባቸው።
13.መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 09-23-39-27-56 (09-17-3-5-90-06)
የገላን አራብሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት