Addis Zemen (Sep 17, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ የተለያዩ የሚወገዱ ንብረቶችን፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሊያሟሉ የሚችሉ ፈላጊዎች መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፤ በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO ) ወይም ቢድ ወንድ፤ ጋር ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ፣ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ፤ ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርበው፤ ብር 500 (አምስት መቶ ብር)፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ በከተማ አስተዳደሩ አካውንት ገቢ በማድረግ፤ መግዛት እና ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ፤ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ፤ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ሥራ ቀናት ዉስጥ፣ በፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዥ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ፤ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ በሌሉበት በዕለቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን፤ የበዓል ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን፣ በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።
- በጨረታ ማስታወቂያ እና በጨረታ ሰነዱ ላይ የቃላት እና የቁጥር ልዩነቶች የሚያጋጥም ከሆነ፤ ቦጨረታ ሰነዱ ላይ ላለው በላይነት ይኖረዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ፤ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ