የኢትዮጵያ ልማት ባንክ (DBE) በሊዝ ፋይናንስ የተገዙ የካፒታል ዕቃዎችን ለመትከል (Installation) እና ሥራ ለማስጀመር (Commissioning) ብቁ የኤሌክትሮ መካኒካል ኩባንያዎችን በግልጽ የፍላጎት መግለጫ (EOD) እንዲያመለክቱ ይጋብዛል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ (DBE) በሊዝ ፋይናንስ የተገዙ የካፒታል ዕቃዎችን ለመትከል (Installation) እና ሥራ ለማስጀመር (Commissioning) ብቁ የኤሌክትሮ መካኒካል ኩባንያዎችን በግልጽ የፍላጎት መግለጫ (EOD) እንዲያመለክቱ ይጋብዛል


Addis Zemen (Sep 17, 2026)

የካፒታል ዕቃዎች ተከላና ኮሚሽኒንግ አጋሮችን

የፍላጎት መግለጫ ማስታወቂያ (Expression of Interest)

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ (DBE) በሊዝ ፋይናንስ የተገዙ የካፒታል ዕቃዎችን ለመትከል (Installation) እና ሥራ ለማስጀመር (Commissioning) ብቁ የኤሌክትሮ መካኒካል ኩባንያዎችን በግልጽ የፍላጎት መግለጫ (EOD) እንዲያመለክቱ ይጋብዛል።

1. የፍላጎት መግለጫው ዓላማ

ባንኩ በኪራይ መልክ ለተበዳሪ ደንበኞች የሚያቀርባቸውን የካፒታል ዕቃዎች የሚተክሉ ብቃትና ልምድ ያላቸውን ተካይ ድርጅቶች ለመለየት እና ለቀጣይ ባንኩ ለሚያስተክላቸው ማሽነሪዎች የተካይ ድርጅቶች አጭር ዝርዝር (Shortlist) ለማዘጋጀት ነው።

2. የሚካተቱ ዘርፎች

  • አጠቃላይ ማኑፋክቸሪንግ
  • አግሮፕሮሰሲንግ
  • ግንባታና የህንፃ ቁሳቁስ ማምረቻ
  • ኃይልና ዩቲሊቲ መሠረተ ልማት
  • ጨርቃ ጨርቅና ልብስ ስፌት
  • ማዕድንና የብረታ ብረት ሥራዎች
  • ኢንዱስትሪያል ማሽነሪዎች
  • የህክምና መሣሪያዎች
  • የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች እና ሌሎች

3. የማመልከቻ መስፈርቶች

አመልካቾች የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማሟላት አለባቸው፦

  • የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የታከስ ክሊራን ሰነድ፤
  • የኩባንያው አጠቃላይ ፕሮፋይል፣
  • የፋይናንስ አቅም ማረጋገጫ፣
  • ተመሳሳይ ሥራዎችን የሠሩበት ልምድ ቢያንስ 2 (ሁለት) ማስረጃ (Project References) የሚያቀርቡ እና
  • የተፈቀደላቸው ሕጋዊ ተወካይ ስም፣ ስልክ ቁጥር እና የኢሜይል አድራሻ

4. የማመልከቻ ማቅረቢያ ሂደት

ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2019 .. (ከሰዓት በኋላ 1000 ሰዓት) ድረስ ለባንኩ የሚቀርቡት ሰነዶች በታሸገ ፖስታ ተደርገው “Expression of Interest for Capital Goods Installation and Commissioning Services” የሚል ግልጽ ርዕስ በመጻፍ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት የካፒታል ዕቃዎች ግዥና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ወይም በባንኩ ቅርንጫፍ/ዲስትሪክት መሥሪያ ቤቶች በአካል መቅረብ አለበት።

5. የምርጫ ሂደት

ባንኩ አመልካቾችን በቴክኒክ፣ በአስተዳደር እና በፋይናንስ ብቃታቸው መሠረት ይገመግማል፤ ተወዳዳሪነታቸው የተረጋገጠና ለአጭር ዝርዝር (Shortlist) ውስጥ የሚገቡት ብቻ በቀጣይ የሚጠሩ ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ

ተቋም፦ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ካፒታል ዕቃዎች ግዥና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት

ስልክ ቁጥር፦ 011-551-1188 / 89 (Ext. 1406)

ማስታወሻ፡ ይህ ማስታወቂያ የውል ስምምነት ጥያቄ (Call for Bid) አይደለም፤ የዚህ ጥያቄ ዋና ዓላማ ለወደፊት ፕሮጀክቶች የሚሆኑ ብቁ አጋር ኩባንያዎችን አስቀድሞ መለየት ብቻ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ