በድሬደዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፑል በስሩ ለሚገኘው ለጽዳትና ውበት ለ2019 በጀት አመት ለስራ የሚያገለግሉ የጽዳት ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በድሬደዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፑል በስሩ ለሚገኘው ለጽዳትና ውበት ለ2019 በጀት አመት ለስራ የሚያገለግሉ የጽዳት ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Melekite Dire (Sep 23, 2026)

 የጨረታ ማስታወቂያ

በድሬደዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፑል በስሩ ለሚገኘው ለጽዳትና ውበት ለ2019 በጀት አመት ለስራ የሚያገለግሉ የጽዳት ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ጨረታውን መወዳደር ለምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ መስፈርት፡–

  1. በዘርፉ የተሰማራ የንግድ ፈቃድ ያለው
  2. የዘመኑን ግብር የከፈለ
  3. የግብር ከፋይነተ መለያ ቁጥር (Tin No) ያለው
  4. የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
  5. የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
  6. በመ/ቤቶች መልካም አፈፃጸም ያለው
  7. የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ) በ CPO በባንክ የተረጋገጠ ማስያዝ ይኖርባቸዋል
  8. መ/ቤቱ ባዘጋጀው ጨረታ ሰነድ ላይ በአቅራቢነት መሞላት ያለበት እያንዳንዱ የሰነድ ክፍል ተሞልቶ የተጫራቾች ፊርማና ማህተም ከሌለው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  9.  ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሰነድ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የፑሉ ፋይናስ ክፍል መግዛት ትችላላችሁ
  10. ጨረታው በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀን አየር ላይ ውሎ በ22 ተኛ ቀኑ ይከፈታል በዚያው ቀን 3፡30 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል።
  11. የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባችሁ

ማሳሰቢያ መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለበለጠ መረጃ በስ/ቁ 0915755324

አድራሻ፡– የድሬደዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ቢሮ (ቴሌ ትራፊክ መብራት አጠገብ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *