Be'kur (Sep 28, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር በ2019 በጀት አመት ለአገልግሎት የሚውሉ
- ሎት1.የማገዶ እንጨት፣
- ሎት2. የዳቦ አቅርቦት፣
- ሎት3. የምግብ ምርቶች እና
- ሎት4.የእህል ምርት ውጤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ።
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ። የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና የድርጅቱ ህጋዊ
- ማህተም ያላቸው።
- የጠቅላላ ግዥ መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም የእቃ ግዥ ከብር 20,000 (ሃያ ሺህ ) በላይ እና ለአገልግሎት ከ10,000.00 (አስር ሺ ) ብር በላይ ሶስት በመቶ ቅድመ ግብር የሚቀነስ ይሆናል።
- የእቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ የውልማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ አስር (10) በመቶ በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ ማህተም በማድረግ ፣የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ ቲን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ሰነድ የተገዛበት ደረሰኝ ኮፒ በአንድ በታሸገ ፖስታ እና በሌላ ፖስታ ኮፒ በማድረግ በፖስታው ላይ ኮፒና ኦርጅናል ብለው በመጻፍ ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ፖስታ ተደርጎ በት/ቤቱ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- ለጨረታ ሰነድ ለመግዛት ብር 200 (ሁለት መቶ ) ከት/ቤቱ ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድግ ሰነድ መግዛት አለባቸው።
- ጨረታው ከመስከረም 18/2019 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በጋዜጣ ታትሞ ይቆያል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን መስከረም 28/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል። ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ወይም ኮሬክሽ ካለው ፍሉድ መጠቀም አይፈቀድም።
- ት/ቤቱ በሚቀርቡ እቃዎች ላይ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ሲሆን፤ እቃዉን በራሱ የትራንስፖርት ወጭ እና የጫኝ አውራጅን ወጭ ታሳቢ በማድረግ የሚወዳደር ሲሆን በወቅቱ ሀዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ማቅረብ አለበት።
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 መሰረት ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል፡
- አድራሻ ደ/ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግቢ ስልክ 09 20 50 43 80/ 09 20 50 68 87/ 09 37 37 28 10 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡።
ሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት