የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 07, 2026)

የዝግ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ለአቶ ሙሐመድ ቦራ በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሰረት የኪራይ ክፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ

የተከራዩ ስም

የሚሸጠው ንብረት ዓይነት እና ዝርዝር መረጃ

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የዝግ ጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር)

ዝግ ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ

የዝግ ጨረታ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

የጨረታ ሁኔታ

1

አቶ መሐመድ ቦራ

1. Rotary Oven 14 Try (01) set 2.Volumetric Dough Divider PAT ማከፋፈያ (01) set. 3. Mixer የሊጥ መቀላቀያ (01) set 4. Molding machine የሊጥ ቅርጽ ማውጫ (01) set 5. Brade slicer የዳቦ መቁረጫ አንድ (1) set 6. French tray with trolley ሁለት (02) set 7. Flat tray with Trolley ሁለት (02) 8. Diesel Generator አንድ (01) set ናቸው፡፡

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በቡርጂ ዞን፣ ሶያማ ከተማ አስ/ር፤ 02 ቀበሌ ክልል ውስጥ በተቋቋመው በአቶ መሐመድ ቦራ (በተከራይ) የዳቦ ማምረቻ ቦታ፤

7,237,089.33

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጋሞ ዞን፣ አርባምንጭ ከተማ በሚገኝው የዲስትሪክቱ ቢሮ

ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 እስከ 6፡00

ዝግ ጨረታ

የዝግ ጨረታው መመሪያ

1. በዝግ ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስምና አድራሻ በመጥቀስ፤ የታደሰ መታወቂያ ኮፒ፤ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25% በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ገዢው የሚገዘበትን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል፡፡

2. ንብረቱ የሚገኘው ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በቡርጂ ዞን፣ ሶያማ ከተማ አስ/ር፤ 02 ቀበሌ ክልል ውስጥ በተቋቋመው በአቶ መሐመድ ቦራ (በተከራይ) የዳቦ ማምረቻ ቦታ፤ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው፡፡ የዝግ ጨረታ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ፤ ንብረቶችን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነጻ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት/በሕግ የተወሰነ ታክስ ጨምሮ የሚጠየቁ ማንኛውንም ክፍያ በቅድሚያ በመክፈል ንብረቱን ይረከባል፡፡

3. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ/በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን ይረከባል፡፡በዝግ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ ሁሉ በዝግ ጨረታ መሳተፍ ይችላል፡፡

4. ንብረቱን በከፊል ለመከራየት የሚፈልግ ተጫራች ከሆነ ቢያንስ ያሸነፈበትን ዋጋ 20% ቅድሚያ በመክፈልና የባንኩን የሊዝ ኪራይ መስፈርት በሟሟላት በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ የማሽኔሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ግን በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የዝግ ተጫራች አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡ለተሸነፉ ተጫራቾች በጨረታው ያስያዙት የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡

5. ንብረቱ በባንኩ የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀክቱ ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ–ሁኔታዎች መስማማት ይጠበቅበታል፡፡ የዝግ ጨረታ አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን ለማስተዳደር የሚወጡ ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ ይጠበቅበታል፡፡

6. የዝግ ጨረታ አሸናፊ የካፒታል ዕቃው ከለበት ቦታ ወደ ሚፈለግበት ቦታ ማጓጓዣ ወጪ፤ የጉዞ ኢንሹራንስ፤ ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዢው ይከፍላል፡፡

7. የዝግ ጨረታው ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኘበት ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በኢትዮጰያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪከት ሎን ወርክ አውት ዲቪዥን ቢሮ ይደረጋል፡፡

ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጰያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-181-0606/0303 ደውሎ ማነጋገር ይችላል፡፡ ንብረቶቹን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዝግ ጨረታ ቀን በፊት ባሉት ጊዜያት ቀጠሮ በመያዝ ንብረቶቹ በሚገኙበት በተከራይ ማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይቻላል፡፡

ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የዝግ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በተጨማሪም ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *