Reporter (Oct 25, 2026)
ሐካማዝ ኮስሞቲክስና ፕላስቲክ ማምረቻ ኃላ.የተ.የግ ማህበር
የትራንዚተር አገልግልት የጨረታ ማስታወቂያ
ሐካማዝ ኮስሞቲክስ እና ፕላስቲክ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከውጭ ሀገር የሚያስመጣቸውን
- የፕላስቲክ ጥሬ ዕቃዎች (PVC/HDPE)፣ የኮስሞቲክስ ግብዓት ጥሬ ዕቃዎች፤ ማሽነሪዎች እና መለዋወጫዎችን በጅቡቲ ወደብ በኩል (ወደ ሞጆ ወይም ቃሊቲ ደረቅ ወደብ) እንዲሁም
- በአየር መንገድ (በቦሌ ካርጎ) ፈጣንና ቀልጣፋ የጉምሩክ አስተላላፊነትና የማጓጓዝ አገልግሎት (Customs Clearance and Freight Forwarding /Transit Service) የሚሰጡ ብቁ ተወዳዳሪ ድርጅቶችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
ተወዳዳሪዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መሠረታዊ መስፈርቶች፡–
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የጉምሩክ አስተላላፊነት (Transit) የሥራ ፈቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታክስ ክሉራንስ (Tax Clearance) ማቅረብ የሚችለ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሌት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው።
- በማምረቻ ዘርፍ (manufacturing Sector) ካለ ፋብሪካዎች ጋር በተመሳሳይ ምርቶችላይ የላቀ የሥራ ልምድ ያላቸው እና የፋብሪካ የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችለ።
- የወደብ እና የትራንስፖርት ወጪዎችን በራሳቸው አቅም ከፍለው ዕቃውን በፍጥነት የማስለቀቅ የፋይናንስ አቅም (Credit Limit) ያላቸው።
- የጉምሩክ አሠራርን ተከትለው ኮንቴነሮችን በፍጥነት ለማስለቀቅ በቂ እና ብቁ የሆነ የሠው ኃይል ያለው፤
- በሃገሪቱ የሚወጡ ህጎች መመሪያዎች እና አዋጆች ጠንቅቀው የሚያውቁ፤
- ኮንቴነሮቹ ካለአግባብ ከጉምሩክ ግቢ እንዳይቆዩ ኃላፊነት ወስዶ በተወሰነ ጊዜ ለማስወጣት ተጠያቂነት መውሰድ የሚችል
- ድርጅታችንን ወክሎ ከጉምሩክ የሚመጣብንን ጥያቄ መመለስ እና ቀርቦ ማስረዳት የሚችል
የማመልከቻ እና የጨረታ አቀራረብ ሁኔታ፡–
- ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንስ (የዋጋ) ማቅረቢያ ሰነዶቻቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨልፕ (Sealed Envelope) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ባለት የሥራ ቀናት ውስጥ ማመልከቻቸውን ማቅረብ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በአካል በመምጣት ከዚህ በታች በተጠቀሰው የድርጅቱ ዋና ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
የድርጅቱ አድራሻ፡
ሐካማዝ ኮስሞቲክስ እና ፕላስቲክ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ኃይሌ ጋርመንት ላፍቶ ኢንደስትሪ መንደር ከሮሃ ፓክ አጠገብ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ለተጨማሪ መረጃ ስልክ +251 95 533 2977/ 9 13 56 72 46
ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።