Addis Zemen (Oct 27, 2026)
የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች ግልጽጨረታ
ቁጥር ግ11/2010 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 መሰረት የተተዉ ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በአቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 9 መሠረት የተተዉና የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም
- Air compressor፣
- የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማዎች፣
- ሽቶዎች፣ ፔርሙዝ፣ ቻርጀር፣ CASTROL oil ፣Hair straightener እና
- ሌሎች እቃዎች, Passenger Lift እና umbrella እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፤ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ ከኦከሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በመግዛት ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ሲሆን አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ከኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሰነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶችን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ሰአት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 ሰአት እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ሰአት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 መመልከት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን ከኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም /ድረገፅ/ ኦንላይን ላይ ብቻ መግዛት እና መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ በኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ማያያዝ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MOD]O BRANCH OFFICE በሚል ሥም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ ፤አዳማ እና ሞጆ ቅርንጫፎች ብቻ አሰርተው አክሽን ኢትዮጵያ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ባለው የሲፒኦ አማራጮች ኦንላይን ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አስቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን፤ ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፣ በጨረታ ተሸጦ የተወሰደ እቃ ተመላሽአይደረግም። ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም።
- ተጫራቾች የአከሸን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et] ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
- የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 5፡00 ሰአት ድረስ በኦከሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን ፕላትፎርም መወዳደሪያ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደትና ውጤት ኦንላይን መከታተል ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ 15% ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
- ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተጀመረ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፣ በጨረታ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታው ተጀምሮ ዋጋ ከሰጡ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም ። የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
- የግልጽ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
- በተራ ቁጥር 10 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ/ ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።
- አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ የአቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው፡፡ በጨረታ ተሸጦ በጨረታ አሸናፊው የተወሰደ እቃ አይመለስም።
- የኦክሸን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር ስልክ ቁጥር መስመር 9164 ወይም 09-05-11-55-11/011-666-8828 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 022-236-90-94 /022-236-01-90 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት