ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ. የቢሮ ዕቃ ማዛወር አገልግሎት ግዥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ. የቢሮ ዕቃ ማዛወር አገልግሎት ግዥ ይፈልጋል


Reporter (Oct 28, 2026)

ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ.

ለ3ተኛ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ፡

የቢሮ ዕቃ ማዛወር አገልግሎት ግዥ

ቁጥር:- ፀኢ/ግንአ/006/2019

ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአሁኑ ቦታው (ቦሌ ድልድይ  የቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት) ከሚገኘው ቢሮ  አዲስ ወዳስገነባው  ዋና መ/ቤት አድራሻ (አዲስ አበባ ሬስቶራንት ፊት ለፊት፣ ደጃዝማች ውቤ አካባቢ) ለማዛወር ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፣ ኩባንያው የቢሮ ዕቃዎችን (ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮች፣ የኮምፒውተርና የሰርቨር ዕቃዎችን ወዘተ) እና የተለያዩ የኩባንያውን ሰነዶች በጥንቃቄ በማሸግ፣ በመጫን፣ በማጓጓዝ እና በማውረድ/በማደራጀት የተረጋገጠ ልምድ ያላቸውን ብቁ ድርጅቶች በዚህ ክፍት ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

ከተጫራቾች የሚጠየቁ መስፈርቶች፡

  1. ተጫራቾች ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ  የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ፋይናንሻል ተቋማትን ጨምሮ ለትልልቅ ድርጅቶች ተመሳሳይ ስራዎችን በመስራት የ5 ዓመት ልምድ እና አቅም እንዳላቸው እንዲሁም ስራውን ማከናወናቸውን የሚገልጽ ወቅታዊ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች አስፈላጊ የሆኑ የማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን እና የማሸጊያ ቁሳቁሶችን የማቅረብ አቅም ሊኖራቸው ይገባል።
  4. ተጫራቾች ስራውን ለማጠናቀቅ የሚፈጅባቸውን ጊዜ የሚያሳይ የሥራ መርሃ ግብር ማቅረብ አለባቸው።
  5. የጨረታ ማስከበሪያ፡ ተጫራቾች 50,000.00 ብር (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም ያለ ቅድመ ሁኔታ በሚፈጸም የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) ማቅረብ አለባቸው።
  6. አገልግሎት ሰጪው በእንቅስቃሴው ሂደት ለሚደርስ የሰነድ መጥፋት ወይም ጉዳት የኢንሹራንስ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅበታል።

የጨረታ ሂደት፡–

  • የጨረታ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቦሌ ድልድይ የቀድሞ ብራስ ሆስፒታል ፊትለፊት በሚገኘው 3ኛ ፎቅ የኩባንያው  የፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ፣ ከጥቅምት 18/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ድረስ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  • የጨረታ ማስረከቢያ፡ የተሟላ የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  • የጨረታ መክፈቻ፡ ጨረታው ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • የኩባንያው መብት፡ ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • የቢሮቹን ጉብኝት፡ ተጫራቾች የሁለቱንም ሕንፃዎች አቀማመጥ እና የሚዛወሩ ዕቃዎችን አይነትና መጠን ለመገምገም የሚያስችል የቅድመ–ጨረታ የጉብኝት ፕሮግራም ጥቅምት 18-20/2019  በስራ ሰዓት ማየት ይቻላል፡፡

አድራሻ፡– ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤት ቦሌ ድልድይ፣ የቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት

ስልክ፡ +251 111 119 70 / +251 116 50 66 30


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *