Addis Zemen (Oct 31, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት በረከት ማርቆስ እና የፍ/ባለዕዳ ሶፋ መሀመድ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/335203 በህዳር 19 ቀን 2018ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/344458 በ28/05/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በሞጆ ከተማ አስ/ጽ/ቤት በሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤ ግቢ ውስጥ የሚገኝ የቡና መፈልፈያ ፕላንት( 10 TPH Coffee beans processing plant) የሆነ ንብረት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 34,719,382.68 ( ሰላሳ አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ አስራ ዘጠኝ ሺህ ሶስት መቶ ሰማንያ ሁለት ከ68/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 17 ቀን 2019ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታውቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፣እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/እፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን መንገድ በሐራጅ ስለመሽጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌደራል ፍ/ቤት የፍርድ አፈፃጸም ጽ/ቤት