በምስራቅ ጐጃም ዞን የማቻከል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ዉስጥ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን ግዥ መፈጸም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በምስራቅ ጐጃም ዞን የማቻከል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ዉስጥ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን ግዥ መፈጸም ይፈልጋል


Be'kur (Nov 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምስራቅ ጐጃም ዞን የማቻከል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ዉስጥ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን ማለትም፡- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች፣ ሎት 3. ኮምፒዉተር እና ተዛማጅ፣ ሎት 4. የዉጭ ፈርኒቸር፣ ሎት 5. የአፈር ማጓጓዝ አገልግሎት፣ ሎት 6. ኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ሎት 7. ክሎሪን፣ ሎት 8. የስፖርት እቃዎች፣ ሎት 9. የስፖርት አልባሳትና ጫማዎች ለመግዛት እንዲሁም ሎት 10. አማሪ የወበሽ ቀበሌ የገበሬዎች ማሰልጠኛ ተቋም ግንባታ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ 

በመሆኑም፡

1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለግንባታ ጨረታ ለ25 ተከታታይ ቀናት ለሌሎች ጨረታዎች ደግሞ ለ10 ተከታታይ  ቀናት   በጋዜጣ ይቆያል፡፡

3. የጨረታ ሰነዱን በማቻከል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የተዘጋጀውን የዕቃዉን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ስለሆነም በዋጋ መሙያዉ ላይ ሥርዝ ድልዝ በግልጽ የማይነበብ  በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ያቀረበ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡

4. ሰነዱን በጥንቃቄ ሞልቶ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን አድራሻ  ህጋዊ ማህተም፣  ሙሉ ስምና ፊርማ በመፃፍ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለግንባታ ጨረታዉ  እስከ 26ኛው ቀን ለሌሎች ጨረታዎች እስከ 11ኛው ቀን  እስከ ረፋዱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. ተወዳዳሪዎች የሚሰጡት ዋጋ ከብር 500‚000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃ ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት ቁጥር, 1 ,2 እና 3 ብር 50,000 (ሃምሳ  ሽህ ብር) ለሎት ቁጥር 4,5,6,8 እና 9 ብር 20,000 (ሃያ ሽህ ብር)  ሎት ቁጥር 7 ብር 5,000 (አምስት ሽህ ብር) ብቻ እና ሎት ቁጥር 10 ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር)  በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ውድድሩ በምድብ ሎት በጥቅል ድምር ዋጋ የእያንዳንዱ ሎት አሸናፊ የሚለይ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተዘረዘሩት እቃዎች መካከል አንዱንም እቃ ሳይሞላ ቢቀር ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡

8. መ/ቤቱ  በውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር 20 በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ የማለት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9. ተጫራቾች በሚፈጥሩት ስህተት ለሚከሰተዉ የገንዘብም ሆነ የጉልበት ኪሳራ ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡

10. በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው አይነትና (ስፔስፊኬሽን) መሰረት በትክክል ተሞልቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

11. የገበሬዎች ማሰልጠኛ ተቋም ግንባታ ተጫራቾች ደረጃ GC/BC 7 እና በላይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

12. አሸናፊ ተጫራቾች የአሸነፉትን እቃ ከተማው ውስጥ ባሉት ሴ/መ/ቤቶች ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡

13. ጨረታዉ ለሎት ቁጥር 10 በ26ኛዉ ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጐ ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ለሌሎች ሎት ቁጥሮች በ11ኛ ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጐ ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ በዚሁ እለት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጐ ከረፋዱ በ4፡00 ተጫራቾች  ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 777 04 80 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የማቻከል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት