በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 13, 2026)

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚሆን ሎት 01. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 02. ለንብ ማምረት የሚያገለግሉ እቃዎች ሎት 03. የችግኝ ማምረቻ መሣሪያዎች መገልገያ ግብዓቶች 04. ቋሚ እቃ ፈርኒቸር ሎት 05. ቶሎ ቶሎ የሚያልቁ የመኪና እቃዎች ሎት 06. የደንብ ልብስ አልባሳት ሎት 07. የደንብ ልብስ ጫማ ሎት 08. የመኪና ዘይትና ቅባት ሎት 09. ባለ 3 እግር የትራንስፖርት ባጃጅ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ሰነዱን በማየት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸው።

2. የግዥ መጠኑ ከብር 500,000/አምስት መቶ ሽህ ብር / በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።

3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራች ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 9 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO ብቻ የጠቅላላ ዋጋውን 1% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

5. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 በመምጣት በመክፈል ከ4/03/2019 ዓ.ም እስከ 13/4/2019 ዓ.ም 11፡30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ።

7.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 114 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ከ4/03/2019 ዓ.ም እስከ 13/4/2019 ዓ.ም 11፡30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ። የጨረታ ሳጥኑ በ14/03/2019 ዓ.ም ከጧቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል። ይሁን እንጂ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነና የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው የመክፈቻ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

8. የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም፤ ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ።

9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው አሠሪው መሥሪያ ቤት ጋር ከጨረታ መክፈቻ ከ 5/አምስት/ ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 65 06 14 05 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

10. የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ ይኖርበታል። ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ዉድድር ውጭ ያስደርጋል።

11. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ጊዜ በኋላ ለ45 ቀናት ይሆናል።

12. ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆንና ለወደፊቱም በመሥሪያ ቤቱ ግዥ የማይሳተፍ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ ይሆናል።

13. ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊው ተጫራች በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20% (ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል ይሆናል።

14. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል። 

15. ለሎት 6 ለሎት 07 እና ለሎት 8 መምሪያው ሳንፕል የሚያቀርብ ይሆናል።

16. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ