በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ስልጠና ቢሮ የቅዱስ ላሊበላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለቢሮ፣ ለግንባታ፣ ለማሰልጠኛ፣ ለብቃት ምዘና ማስመዘኛ እና ለተለያዩ ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 27, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ስልጠና ቢሮ የቅዱስ ላሊበላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለቢሮ፣ ለግንባታ ፣ ለማሰልጠኛ ፣ ለብቃት ምዘና ማስመዘኛ እና ለተለያዩ ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን እቃዎች፡-

ምድብ

የንግድ ስራ መስክ

ሎት 1

የጽኅፈት መሳሪያዎች

ሎት2

ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች

ሎት3

ኮምፒዩተር፣ የኮምፒዩተር መሳሪያዎችና ተጓዳኝ እቃዎች

ሎት4

የንፅህና መጠበቂያና የኮስሞቲክስ እቃዎች

ሎት5

የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች

ሎት6

የግንድላና አጠና (የጣውላ፣ ኮምፒስታቶና ሌሎች ተዛማጅ ምርቶች ጨምሮ )

ሎት7

የጨርቃ ጨርቅ ጭረቶች ፣ ጨርቃጨርቅ፣ ጥጥ፣ ከርና አልባሳት ችርቻሮ ንግድ

ሎት8

ጫማና የቆዳ ውጤቶችና ተዛማጅ

ሎት9

የኤሌክትሪክ መሳሪያዎችና ተዛማጅ እቃዎች

ሎት10

የኢንዱስትሪ፣ የግብርናና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችና መገልገያዎች

ሎት11

ሱፐር ማርኬት

ሎት12

አትክልትና ፍራፍሬ(የተዘጋጁትንም ጨምሮ)ምርቶች

ሎት13

የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ማስዋቢያዎችና መገልገያዎች

ሎት14

የመንገድና የደረቅ ጭነት አገልግሎት

ሎት15

የህትመት ተዛማጅና ስራዎች

ሎት16

የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች ተከላና ጥገና

ሎት17

ማሽነሪና የማሽነሪ መለዋወጫ እቃዎች

ሎት18

የማሽነሪ ኪራይ

ሎት19

የግንባታ ቦታ የማፅዳትና የማዘጋጀት ስራ

ሎት20

የእንስሳት መኖና ጥሬ እቃዎች

ሎት21

የእንስሳት መድሃኒቶችና የህክምና መገልገያዎች

ሎት22

የቤትና የቢሮ እቃዎች ጥገና

ሎት23

መጠጥ ችርቻሮ

ሎት24

የምግብ ምርቶች

 

 

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር  የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በየምድቡ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው እና ጠቅላላ ዋጋው ከብር 200000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ለሆነ ግዥ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለበት።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይቻላል።
  3. ተጫራቾች የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚሆን የብር መጠን በጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 5 በመምጣት ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል።
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በሚታሰብ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጐ ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3፡30 ላይ ይከፈታል። 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ወደ ቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይተላለፋል።
  7. የሚገዙ የእቃዎችንና አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 336 1013 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

የቅዱስ ላሊበላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *