Your cart is currently empty!
አንበሣ ጫማ አ.ማ አቃቂ ቃሊቲ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች
የጨረታ ማስታወቂያ
አንበሣ ጫማ አ.ማ አቃቂ ቃሊቲ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 2 በሚገኘው ዋናው መቤት በመኘት ተሽከርካሪዎችን ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር በ100 (አንድ መቶ) በመክፈል አቃቂ ከሚገኘው ፋብሪካ የፋይናንስ ዋና ክፍል መሣካት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በካሽ ከሆነ አቃቂ ፋብሪካ በሚገኘው የድርጅቱ ፋይናንስ ዋና ክፍል በመክፈል ደረሰኙን ወይንም ሲፒኦ በማሰራት የምትገቡትን ዋጋ በግልጽ በመጥቀስ የክፍያ ደረሰኙን ሰነድ አያይዛችሁ በዋናው ፋብሪካ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን በማሰገባት መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከቫት በፊትና በኋላ በሚል በግልጽ መጥቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ሌላ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ10 ቀን በኋላ ባለው የስራ ቀን ላይ በ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ወዲያውኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ መሆናቸው በተገለፀላቸው በ 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ተሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ ማንሳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካላነሱ ግን ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ በድጋሚ ጨረታ በማውጣት እንዲሸጥ ይደረጋል፡፡ “አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አንበሣ ጫማ አ.ማ