Your cart is currently empty!
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጉለሌ ፋና የመጀ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018 ዓ.ም.
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጉለሌ ፋና የመጀ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
1ኛ. (ሎት 1) የደንብ ልብስና የስፖርት ትጥቆች፣
2ኛ. (ሎት 2) አላቂ የቢሮና የጽህፈት መሳሪያዎች የተለያዩ የፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ቀለሞች ተዛማጅ ዕቃዎች፣
3ኛ. (ሎት 3) ህትመት፣
4ኛ. (ሎት 4) አላቂ የህክምና መርጃ እቃዎች፣
5ኛ (ሎት 5) አላቂ የትምህርት እቃዎች፣
6ኛ. (ሎት6) አላቂ የጽዳት እቃዎች፣
7ኛ. (ሎት 7) የተለያዩ መሳሪያዎች እና መፃሕፍት፣
8ኛ. (ሎት 8) የማሽን ጥገና፣
9ኛ. (ሎት 9) ለህንፃ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች ጥገና፣
10ኛ. (ሎት 10) ትራንስፖርት፣
11ኛ. (ሎት 11) ለፕላንት ማሽነሪ እና ለመሳሪያዎች፣
12ኛ. (ሎት 12) ቋሚ እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል፣
13ኛ. (ሎት 13) መስተንግዶ፣
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች
በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ(Tin) ቁጥር ያላቸው፡፡
3.የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
4. የአቅራቢዎች ዝርዝር በህጋዊነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ናሙና/ሳምፕል/ ለሚጠይቁ ዕቃዎች ማቅረብ የሚችል፡፡
6. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10% ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ላይ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝና ተዋውለው ዕቃዎችን በትምህርት ቤቱ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ በመግለፅ ዋናውን እና ኮፒውን በመሙላት በሶስት ወይም በአራት በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 09 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ናሙናዎች ጨረታው ከመከፈቱ ከሁለት ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ አካላት ከሆነ ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ጊዜ ከሚመለከተው አካል ወቅታዊ የሆነ፣ በጽ/ቤቱ ስም የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በሚያመርቱት ምርት ብቻ ከሆነ ልዩ አስተያየት ይደረጋል፡፡
11. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ጉለሌ ፋና የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በመገኘት የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር)በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ
- (ሎት 1)፡– 14,586.25 (አስራ አራት ሺ አምስት መቶ ሰማንያ ስድስት ብር 25/ooብር)
- (ሎት 2)፡ 9,600.00 (ዘጠኝ ሺ ስድስት መቶ ብር)
- (ሎት 3)፡– 1,460.00 (አንድ ሺ አራት መቶ ስልሳ ብር)
- (ሎት 4)፦ 240.00 (ሁለት መቶ አርባ ብር)
- (ሎት 5)፡– 1,460.00(አንድ ሺ አራት መቶ ስልሳ ብር)
- (ሎት 6)፡– 9,730.00 (ዘጠኝ ሺ ሰባት መቶ ሰላሳ ብር)
- (ሎት 7)፡ 1,920.00 (አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ ሃያ ብር)
- (ሎት 8)፡– 1,080.00(አንድ ሺ ሰማንያ ብር)
- (ሎት 9)፡– 6,000.00 (ስድስት ሺ ብር)
- (ሎት 10)፡ 1,060.00 (አንድ ሺ ስልሳ ብር)
- (ሎት 11)፡ 9,600.00 (ዘጠኝ ሺ ስድስት ብር)
- (ሎት 12)፡– 2,400.00 (ሁለት ሺ አራት መቶ ብር)
- (ሎት 13)፡– 1,292.70 (አንድ ሺ ሁለት መቶ ዘጠና ሁለት 70/100 ብር) በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ አምጥተው ቢሮ ቁጥር 09 ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
14. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጉለሌ ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት