Your cart is currently empty!
አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ የተለያዩ ምርቶች እና ተረፈ ምርቶች ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የተለያዩ ምርቶች እና ተረፈ ምርቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር -AF/05/2017/Local
አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ምርት እና ተረፈ ምርቶች ማለትም፣
ሎት 1. የጅኦመብሬን ሽት ምርት ውፍረቱ በአማካይ 05 ሚሜ የሆነ
ሎት 2 የኮመን ፕላስቲክ ሽት ምርት ውፍረቱ በአማካይ 0.175 ሚ ሜ የሆነ
ሎት 3 የUPVC PPES ተረፈ ምርት
ሎት 4 የUPVC የጥሬ መያዣ ካኪ ከረጢት
ሎት 5 የጥሬ እቃ መያዣ ፕላስቲክ ከረጢት እና
ሎት 6 ስስ ፌስታል (ነጭ) በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ (መወዳደር) ይችላሉ፡፡
1. ለ2017 ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት (TN Certificate) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች ከላይ በሎት 1፣ 2 እና በሎት 3 ላይ የተገለፁትን እቃዎች ለመግዛት የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የማይችሉ ከሆኑ ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ መንግስታዊ ተቋም የ2017 ለ2018 በጀት ዓመት ግብር ያልከፈለበትን ምክንያት እና በዚህ ጨረታ እነዲሳተፉ የሚፈቅድ ደብዳቤ ለፋብሪካው በመጻፍ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
3. ከላይ በሎት 1 ፣ 2 እና በሎት 3 ከተገለፁት የጅኦመብሬን ሽት ምርት የኮመን ፕላስቲክ ሽት ምርት እና የUPVC PIPES ተረፈ ምርት በስተቀር በሌሎች ሎቶች ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት የንግድ ፈቃድ እና ሌሎች የሕጋዊነት ሠነዶችን ማቅረብ ሳይጠበቅበት በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
4. ተወዳዳሪ ድርጅቶች ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ጨምሮ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
5. ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በፋብሪካው የፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 105 በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር በመክፈል ወይም በኢ-ሜይል (email) አድራሻ amharapipefactory@gmail.com ማግኘት ይችላሉ። አድራሻ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡00-5፡00 ማየት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የሕጋዊነት ሠነዶቻቸውን የመወዳደሪያ ዋጋቸውን፣ የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችን ማስረጃዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 206 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
7. ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15ኛው ቀን ማለትም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 206 ከቀኑ 8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
8. 15ኛው ቀን ሕዝባዊ በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
9. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡትን ምርቶች እና ተረፈ ምርቶችን በአካል በፋብሪካው አድራሻ በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡00-5:00 ማየት ይችላሉ።
10. አሸናፊ ተጫራቾች የውል ስምምነት ለመፈጸም በቅድሚያ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባህርዳር ከተማ ውስጥ ባለ የባንኩ ቅርንጫፍ ማረጋገጫ የተሰጠበት የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በፋብሪካው ስም በማሰራት ማቅረብ አለባቸው።
11. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ለበለጠ መረጃ 09 35-98-37-29/ 09 18-70 18 26 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ
ባህር ዳር