የሰበታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች፣ ደንብ ልብሶች፣ የመኪና ጎማዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018

የሰበታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት 2018 በጀት ዓመት ለከፍለ ከተማው ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ለክፍለ ከተማው ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች፣ ደንብ ልብሶች
  • ሎት 2የመኪና ጎማዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመከፈላቸው በቂ ማስረጃ (ክሊራንስ) ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናትበሲንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር “Sebeta Sub city Finance office “A” 1064814111214* ለእያንዳንዱ ሎቶች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ገቢ በማድረግ ሰበታ ክፍለ ከተማ ገቢዎች በመሄድ ወደ ደረሰኝ በማስቀየር ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰበታ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት መግዛት ይችላል።
  3. ተጫራቾች የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎቶች በተዘጋጀው ሰነድ ብር 35,000.00 (ሰላሣ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ብቻ በሰበታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ /ቤት ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት CPO በጀርባው የባንኩን ማህተም እና ስልክ ቁጥር ከሌላው ተቀባይነት አይኖረውም።
  6. ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ (15%) በመጥቀስ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ ሰነድ ለየብቻ በማሸግ በተባለው ቀን ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተማራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትን(15%) ያካተተ መሆን አለበት።
  8. ለጨረታ በሚያቀርቡት በእያንዳንዱ የሰነዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ስምና አድራሻ የሚገልጽ ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ ማስፈር አለበት።
  9. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሞላቱን በባለሙያ እና ጥራት አጣሪ ኮሚቴ ሲረጋገጥ ብቻ ይሆናል።
  11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ በመጋዘን ቀድመው ማከማቸት ይኖርባቸዋል።
  12. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ የሎት አንድ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙናውን ማቅረብ አለባቸው።
  13. የጨረታው ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 430 የሚከፈት ይሆናል።
  14. ከላይ የተገለጸው የመከፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል።
  15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፦ 011 338 4292

የሰበታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ//ቤት