Your cart is currently empty!
በኢሉባቦር ዞን አልጌ ሣቺ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመኪና እና የሞተር ጎማና የተለያዩ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፣ የግንባታ ዕቃዎች እንዲሁም የተለያዩ ጀነሬተሮች መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢሉባቦር ዞን አልጌ ሣቺ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ከዚህ ቤታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- የጽህፈት መሣሪያዎች
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- የመኪና እና የሞተር ጎማና የተለያዩ መለዋወጫ ዕቃዎች
- የፈርኒቸር ዕቃዎች
- የሰራተኞች ደንብ ልብስ እና የስፖርት ልብስ
- የግንባታ ዕቃዎች
- የተለያዩ ጀነሬተሮች
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችል እና የቫት WAT/ ተመዝጋቢ የ2017 ዓ.ም መሆን አለበት፡፡
- በንግድ ሚኒስቴር በአቅራቢነት ዝርዘር የተመዘገበ፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ 30,000.00/ ሰላሣ ሽህ/ ብር በሲፒኦ / cpo/ ለእያንዳንዱ ዶክመንት ማስያዝ የሚችልና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ / cpo /ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈ ቀርቦ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ የሆነና ዕቃዎቹን በራሱ ሙሉ ወጪ በታዘዘ በ15 ቀን ውስጥ እስከ ጽ/ቤቱ ለማቅረብና ቆጥሮ ማስረከብ አለበት፡፡
- ተጫራቹ የዕቃውን ሞዴል ባልተገለጸበት ቦታ በጨረታው ዝርዝር ላይ አብራርቶ መግለጽ አለበት፡፡
- ተጫራቹ የተፈለገውን ዕቃ ጥራትና ብዛት አሟልተው የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- በፈርኒቸር ዕቃዎች ላይ የምትወዳደሩ ድርጅቶች የፈርኒቸሮችን ዲዛይን ከዋጋው ጋር ማቅረብ እና ካሸነፈ ገጣጥሞ ማስረከብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቹ ለሚያቀርባቸው የደንብ ልብሶች፡- የላፕቶፕ ቦርሳዎች ለመ/ቤቱ አስፈላጊ ለሆኑ ዕቃዎች ሳምፕል /ናሙና/ ማቅረብ ኣለበት፡፡
- ተጫራቹ የሚያቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ5/13/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቆ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢሉባቦር ዞን አልጌ ሣቺ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከግዥ ክፍል 13 ቁጥር በመቅረብ የዕቃዎቹን ዝርዝር እና ለዚሁ የተዘጋጀዉን የተጫራቾችን መመሪያ ሰነድ መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ ሶስት መቶ/ 300.00/ ብር ከኢሉባቦር ዞን አልጌ ሣቺ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዢ ክፍል 13 ቁጥር በመግዛት የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ከልክል ነው።
- የሚወዳደሩበትን ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው እና የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
- ተወዳዳሪዎች ዋጋን የሚገልጽ ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ ፍቃድንና የተለያዩ ተፈላጊ ሰነዶችን የሚገልጽ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም ሲፒኦ/ CPO/ ለየብቻ በ5/አምስት/ ፖስታዎችን በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታው ሣጥን በግዥ ክፍል ቁጥር 13 ውስጥ ክፍት መሆኑን አውቃችሁ እስከ 6ኛው ቀን 4:00 ፖስታዎችን በፈለጋችሁት በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች በኦርጅናል ፈንታ ኮፒ አድርገው የተለያዩ የዕቃ ዓይነቶች መወዳደር ይችላሉ፤ (ለምሣሌ computer፣ Lap Top HP, Note Book Lenevo)፣ ቀለሞችን፣ ጎማዎችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን የመሳሰሉትን በተለየዩ ገጽ ፎቶ ኮፒ በመሙላት መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- VAT 7.50 % እና TOT 2% ከሚገዛዉ ዕቃ የሚቆረጥ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የደንብ ልብስ ጨርቅ ናሙና ከፖስታው ጋር አሽጎ ማቅረብ አለበት። ለተጨማሪ መረጃ ስስክ ቁጥር 0913 357 097 ወይንም 0917 273 702
በኢሉባቦር ዞን አልጌ ሣቺ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Electrical, cttx Energy, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Generators cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Sport Materials and Equipment cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Power and Electricity cttx