የአጋዝያን ቁ.3 2ኛ ደ/ት/ቤት አላቂ የት/ት እቃዎችን፣ አላቂ የጽዳት እቃዎችን፣ የደንብ ልብስ፣ የቢሮ እቃዎች፣ የፎቶ ኮፒ ቀለሞች እና የስፖርት እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 01/2018 /ም

የአጋዝያን .3 2 //ቤት 2018/ በጀት ዓመት የሚከተሉት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1- አላቂ የት/ እቃዎችን፣ አላቂ የጽዳት እቃዎችን፣ የደንብ ልብስ፣የቢሮ እቃዎች፣ የፎቶ ኮፒ ቀለሞች፣ የስፖርት እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • በዚህም መሰረት በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።
  • ከተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ እንዲሁም የንግድ መለያ ቁጥር Tin number) ማቅረብ ይኖርባዋል።
  • በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ የንግድ ምዝገባ ማስረጃ ያለቸውና ባቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ።
  • የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  • በመንግስት ጨረታ ላይ የመሳተፍ ጊዜ ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግሉ የሚመረቱበትን የእቃ ዋጋውን ብር 10,000.00/አስር ብር/ በጽሕፈት ቤቱ ስም የተዘጋጀ (ሲፒኦ) ወይም ጽሕፈት ቤቱ ፋይናንስ በካሽ በማስያዝ ማረጋገጡን ከመወዳደሪያው ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ማንኛውም ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ናሙና ጨረታ ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  • በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10 ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • የምታስገቧቸው ሰነዶች ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይገባም፣ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ውድቅ ነው የሚሆነው።
  • የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡበትን የጨረታ ሰነድ ከታሸገ ኤንቨሎፕ ኤጅናልና ኮፒ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ከሚሸጠው የጨረታ ስነድ ላይ የሚገለፅ የእቃ ብዛት የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው የሚሰሩ ነጋዴዎች የድጋፍ ደብዳቤ ስታመጡ ደብዳቤው በጽ/ቤቱ ኃላፊ ቲተርና ፊርማ ተፈርሞ ማምጣት ግዴታ ነው
  • ከላይ የተጠቀሱት እቃዎች ዝርዝር የሚያሳውቅና የግዥ መመሪያ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር በመክፈል ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት /////ቤት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የተጻፈ ሰነድ አጋዝያን .3 2 ደረጃ /ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጋዜጣው በወጣበት በ11ኛው (በአስራ አንደኛው) የስራ ቀን ጨረታው በዕለቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ 430 ላይ ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአጋዝያን 3 2 ደረጃ /ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል።

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ የግዥ ዘዴ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው መሰረዝ ይችላል።

አድራሻ፡ጎጃም በረንዳ (ሀግቤስ) አቢሲኒያ ባንክ አጠገብ

ተጨማሪ ማብራሪያ፡

በስልክ ቁጥር 0111-1101-23/0111-11-42-10 ደው መጠየቅ ይችላሉ።

በአራዳ ክፍለ ከተማ //ቤት የአጋዝያን .3 2 ደረጃ /ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት