በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኘው የመሿለኪያ ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኘው የመሿለኪያ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት- 1 መድኃኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት ግዥ
  • ሎት- 2 የሥራ መገልገያ የደንብ ልብስ ግዢ እና የደንብ ልብስ ስፌት
  • ሎት- 3 የጽሕፈት መሳሪያ እና አላቂ የፅዳት እቃዎች ግዥ
  • ሎት- 4 የቢሮ መገልገያ ቋሚ እቃ እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ
  • ሎት- 5 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ግዥ
  • ሎት- 6 የላብራቶሪ ህከምና መሳሪያዎች ጥገና
  • ሎት- 7 የተለያዩ ህትመቶች
  • ሎት- 8 የካልብሬሽን ሰርቪስ አገልግሎት
  • ሎት- 9 የጤና ጣቢያው አጠቃላይ የግቢ እድሳት ሥራ
  • ሎት- 10 የጀነሬተር እና የላውንደሪ ማሽን ጥገና
  • ሎት- 11 የCPD አሠልጣኝ ባለሙያ ሥራ
  • ሎት- 12 ለመስተግዶ አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች

ለመግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የታክስ ግዴታውን የሚያመላክቱ ሰነዶች፣ የአቅራቢነት ምዘገባና የምስክር ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ እና አነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት የድጋፍ ደብዳቤ ማስረጃ በግልፅ የሚታይ ፎቶኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

እያንዳንዱ ተጫራች የሚወዳደርበትን እቃ ዋጋ እስከነቫቱ መሙላት ይኖርበታል። ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት በትክክል በመሙላትና በታሸገ ፖስታ ወይም ኢንቬሎፕ በማድረግ የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በተናጥል አሽገው የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ በመሿለኪያ ጤና ጣቢያ የግዥ ክፍል በር ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

  • ለሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሠላሳ ሺ ብር )
  • ለሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ 15,000 (አሥራ አምስት ሺ ብር)
  • ለሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ 20,000(ሃያ ሺ ብር)
  • ለሎት- 4 የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 ( ሠላሳ ሺ ብር)
  • ለሎት- 5 የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 (አምሰት ሺ ብር)
  • ለሎት- 6 የጨረታ ማስከበሪያ 7,500 ( ሰባት ሺ አምስት መቶ ብር)
  • ለሎት- 7 ጨረታ ማስከበሪያ 5,000 ( አምስት ሺ ብር) 
  •  ለሎት- 8 የጨረታ ማስከበሪያ 3,000 ( ሦስት ሺ ብር)
  • ለሎት- 9 የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሠላሳ ሺ ብር)
  •  ለሎት -10 የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 (አምስት ሺ ብር )
  • ለሎት- 11 የጨረታ ማስከበሪያ 3,000 (ሦስት ሺ ብር )
  • ለሎት -12 የጨረታ ማስከበሪያ 3,000 (ሦስት ሺ ብር) በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

 

  • የጨረታ ማስከበሪያው አሸናፊዎች ተለይተው ውል እስኪፈፀም ድረስ እንደተያያዘ ይቆያል። ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ከ7 ቀን በኋላ 10% የውል ማስከበሪያ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚደርስ ማንኛውም ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለሳል፤ መስሪያ ቤቱ የጨረታውን 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል።
  • የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን እቃ በራሱ የትራንስፖርት ወጪ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል
  • ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ላይ ታሽጎ በዛኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ቢሮ ቁጥር 38 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • በ11ኛው ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
  • የጨረታውን ሰነድ በመሿለኪያ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 07 ረዳት ፋይናንስ ኦፊሰር ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው እቃዎች ጤና ጣቢያው ባዘጋጀው እስፔስፍኬሽን መሠረት ሲሆን ለሁሉም እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

አድራሻ፡- ደብረዘይት መንገድ ቴሌ ጋራዥ ፊት ለፊት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ

ማሳሰቢያ፡- ይህ ሰነድ ሙሉ በሙሉ ወይም ከክፍል 1 እና 7 ውጭ ያሉት ገጾች ኮፒ በማድረግ የሚጠይቀውን መጠይቅ በመሙላት እያንዳንዱ ገጽ ላይ በመፈረም ፤ የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ መመለስ አለበት፣ ማሳሰቢያው ተግባራዊ ካልሆነ የሚቀርበው ጐደሎ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- ግዥ ክፍል በስልክ ቁጥር 011 470 0810 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኘው የመሿለኪያ ጤና ጣቢያ