የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሜይዴይ ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ የመ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ጥር ሜ 001/2018 ዓ.ም.

የአዲስ ከተማ /ከተማ የሜይዴይ ቅድመ 1 እና 1 የመ///ቤት የበጀት አመቱ በግልጽ ጨረታ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።

  1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችና የቢሮ ዕቃዎች  ሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ ( 1%) 3000.00ብር
  2. የደንብ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ           ሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ ( 1%) 4000.00 ብር
  3. የተለያዩ አላቂ የፅዳት እቃዎች              ሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ ( 1%) 3000.00 ብር
  4. አላቂ የህክምና እቃዎች                   ሎት 4 የጨረታ ማስከበሪያ ( 1%) 3000.00 ብር
  5. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች                     ሎት 5 የጨረታ ማስከበሪያ ( 1%) 3000.00 ብር
  6. የተለያዩ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች            ሎት 6 የጨረታ ማስከበሪያ ( 1%) 8000.00 ብር
  7. የህትመት ስራዎች                      ሎት 7 የጨረታ ማስከበሪያ ( 1%) 3000.00 ብር
  8. የተለያዩ ጥገና ስራዎች                  ሎት 8 የጨረታ ማስከበሪያ ( 1%) 6000.00 ብር
  9. የመስተንግዶ ውሀና ቆሎ               ሎት 9 የጨረታ ማስከበሪያ ( 1%) 2000.00 ብር
  10. የደንብ ልብስ ስፌት ዋጋ             ሎት 10 የጨረታ ማስከበሪያ ( 1%) 4000.00 ብር
  11. የካፌ አገልግሎት                     ሎት 11 የጨረታ ማስከበሪያ ( 1%) 3000.00 ብር

በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ

  • ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን 2017. የታደሰ የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው የግዥ ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ወረቀት ያለው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፡፡ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ጨረታው ከመከፈቱ 3ቀን በፊት ናሙናውን በዝርዝር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታውን የሚያቀርበው እና የሚፈፅመው ወኪል ከሆነ ከፍ/ቤት የተሰጠውን ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።
  • ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10  ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 350(ሶስት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ሲመልሱ ሰነዱ ላይ እያንዳንዱ ገፅ ላይ ማህተምና ፊርማ መሞላት ያለበት ተሞልቶ መመለስ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ሲያቀርቡ ቫትን ያጠቃለለና በምንሰጣቸው የዋጋ ቅፅ መሆን አለበት ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አሟልተው ዋናውንና ኮፒውን የመወዳደሪያ ዶክመንት በታሸገ 4 (አራት) ፖስታ በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እስከ 10ኛው የስራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 330 ተዘግቶ 400 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች በአጠቃላይ ዋጋ ብር 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከት/ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  • ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ራሳቸው በሚያመርቱት ምርት መሆን አለበት ካደራጃቸው ወረዳ የጨረታ ማስከበሪያ ህጋዊ ደብዳቤ(CPO) እና የውል ማስከበሪያ 10% በተጨማሪም ያፀደቀው አካል ህጋዊ ማንነት በመግለጽ መወዳደር እንዲችሉ እየገለፅን ሰነዱን በመውሰድ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ የእቃዎችን ዝርዝር ዋጋ እና አይነት በመግለፅ የሰነዱን ፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
  • /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ ማብራሪያ ስልክ፡-011 2 31 01 18/ 0112 13 74 56

አድራሻ፡መርካቶ ጎጃም በረንዳ የድሮው ፋሲል ፋርማሲ ጎን (ከይርጋ ሀይሌ ህንፃ ከፍብሎ)

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ  የሜይዴይ ቅድመ 1 እና 1 የመ///ቤት