Your cart is currently empty!
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የላሊበላ ከተማ አስ/ር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ በተፈቀደ የሥራ ማስኬጃና ካፒታል በጀት የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የቀላል መኪና ጎማ፣ የአዳራሽ መስኮት መጋረጃ፣ ፈርኒቸር፣ የስፖርት ትጥቅ፣ የስፖርት ዕቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎችና አገልግሎት ሰጪዎች በግልጽ ጨረታ በሎት /በጥቅል/ አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የላሊበላ ከተማ አስ/ር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ በተፈቀደ የሥራ ማስኬጃና ካፒታል በጀት የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የቀላል መኪና ጎማ፣ የአዳራሽ መስኮት መጋረጃ፣ ፈርኒቸር፣ የስፖርት ትጥቅ፣ የስፖርት ዕቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎችና አገልግሎት ሰጪዎች በግልጽ ጨረታ በሎት / በጥቅል/ አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. የጨረታው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን ከብር 200,000 በላይ ከሆነ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች፣ የንግድ ፈቃዱን በጀርባው ያለውንም ጭምር ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ነሐሴ 28/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 7/2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጽ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 9 ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን አንዱን ሰነድ በብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን ዋና እና ቅጅ ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በላሊበላ ከተማ አስ/ር ገንዘብ ጽ/ቤት የጨረታ ኮሚቴው ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን መስከረም 8/2017 ዓ.ም ድረስ በማስገባት በ4፡00 ታሽጎ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
6. ከላይ የተጠቀሰው የጨረታ የመክፈቻ ቀን ካላንደር ዝግ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ የመክፈቻው ቀን ለሚቀጥለው የስራ ቀንና ሰዓት ይተላለፋል፡፡
7. የጨረታውን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ለጽህፈት መሳሪያዎች ብር 15,000፣ ለጽዳት ዕቃዎች ብር 900፣ ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 8000፣ ለተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ብር 4000፣ ለቀላል መኪና ጎማ ብር 25,000፣ የአዳራሽ መስኮት መጋረጃ ብር 7,000፣ ፈርኒቸር ብር 5,000፣ የስፖርት ትጥቅ ብር 2,000፣ የስፖርት ዕቃዎች ብር 2,500 በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ /በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማቅረብ ለደህንነት ሲባል የመጀመሪያው ሲሆን አስገዳጅ ሆኖ ከተገኘ ግን በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይቻላል፡፡
9. አሸናፊው አካል አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ 10% በጥሬ ገንዘብ (በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲፒኦ)፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
10. አሸናፊው በላሊበላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ትዕዛዝ መሰረት ያሸነፈበትን ጥራት ያለው ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት በከተማ አስተዳደሩ ንብረት መጋዘን ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ጥራታቸው ጽ/ቤቱ በሚያቀርበው ባለሙያ የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
11. ተጫራቾች ከዚህ በፊት ጨረታ አሸናፊ ሆነው እንደውላቸው ያላጠናቀቁ ወይም ከታወቀ ተቋም ዕገዳ የተደረገባቸውን አያካትትም፡፡
12. ተጫራቾቹ በጨረታው ላይ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ካላቸው የጨረታው የጊዜ ገደብ ከማለቁ ከ3 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 336 1142/ 033 336 1143/033 361 169 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአብክመ የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት