የተለያዩ ንብረቶች ፋይቨር ኦፕቲክስ (fiber optics ) ኬብል፣ የኮንስትራክሽን፣ ፍሪጅ፣ ጀኔረተር፣ ኮንቲነሮች እና የኃይል አስተላላፊ የኤሌክትሪክ ሽቦዎች ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen(Sep 09, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ኒያና አገልግሎትና ትሬዲግ /የተ//ማህበር እና የፍ/ባለዕዳ ኤስዲ ኮንስትራክሽን /የተ//ማህበር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ /ቤት በመ/ቁጥር 325847 9/10/17 / እና በኮ///343753 16/11/2017 . በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ያረፈበት ንብረት የሚገኘው በአቃቂ ቃሊቲ /ከተማ ወረዳ 7 የቤት ቁጥር አዲስ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶች ፋይቨር ኦፕቲክስ (fiber optics ) ኬብል፣ የኮንስትራክሽን፣ ፍሪጅ ጀኔረተር፤ ኮንቲነሮች የኃይል አስተላላፊ የኤሌክትሪክ ሽቦዎች የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 5,254,000 (አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ አራት ሺህ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 23 ቀን 2018 . በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 930 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱን ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ 330 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ// ስም CPO አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም /ቤት