Your cart is currently empty!
ሉሲ ኢንሹራንስ (አ.ማ) የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን በአደጋ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች እና ልዩ ልዩ ቅሪቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2018
ሉሲ ኢንሹራንስ (አ.ማ) የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን በአደጋ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች እና ልዩ ልዩ ቅሪቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች ልዩ ልዩ ቅሪቶችን አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቃሊቲ መናኸሪያገባ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ንብረት ማከማቻ ግቢ ውስጥ ጷጉሜ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሥራ ሰዓት በአካል በመገኘት ማየት ይችላሉ። ለዚሁ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ 22 ካፒታል ሆቴል ፊት ለፊት ክዋሪት ሙሉ ጥላ ኢንተርናሽናል ኩባንያ አጠገብ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት 5ኛ ፎቅ የሚገኝ ሲሆን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመከፈል መውሰድ ይቻላል።
2. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ልዩ ልዩ ቅሪቶች የጨረታ መነሻውን ዋጋ 10 (አስር በመቶ) ከ1,000.00 / ብር ያላነሰ በሉሲ ኢንሹራንስ (አ.ማ) ወይም በእንግሊዝኛ ሀCY INSURANCE (S.C) ስም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ ቀኑ 5፡30 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 ሰዓት እስከ ቀኑ 10:30 ሰዓት አድራሻው ከላይ በተጠቀሰው ዋና መ/ቤት የባንክ ከፍያ ማዘዣውን (CPO) በማቅረብ በመጫረቻው ቅጽ ላይ የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ማስገባት ይችላሉ።
4. ጨረታው መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በኩባንያው ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ የሪከቨሪ ዋና ክፍል ይከፈታል።
5 አሸናፊ ተጫራቾች በአሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ።
6. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊ ተጫራቾች የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ከሚገዙበት ዋጋ ጋር ይታሰብላቸዋል።
7. ተጫራቾች ጨረታውን ያሸነፉበትን ሙሉ ክፍያ አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ዕለት ጀምሮ በ 5 የሥራ ቀናት ውስጥ በመከፈል ንብረቱን ካልተረከቡ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል።
8. አሽናፊ ተጫራቾች በጨረታ የገዙትን ንብረት ጨረታው በተከፈተ በ 7 ቀናት ውስጥ ከኩባንያው ግቢ ካላወጡ ለ10 ቀናት በቀን ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) የምናስከፍል ሲሆን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ካላነሱ በሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ።
9. ለጨረታ በቀረቡት ንብረቶች ላይ የሚፈለግ ማንኛውም ዓይነት ወጪዎችን የጨረታ አሸናፊው ይከፍላል።
10. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው።
11. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114704981/0911634013/0913014519 በመደወል ማነጋገር ይችላሉ።