Your cart is currently empty!
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ በቢሮ፤ ዞን፤ ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፤ ትራክተር አና ሞተር ሳይክሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 17, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 03/2018
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ በቢሮ፤ ዞን፤ ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፤ ትራክተር አና ሞተር ሳይክሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 11 /2018 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤
1. የኤጀንሲው አድራሻ፤ አዲስ አበባ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ/የኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት/ ጫፌ አናኒ ህንጻ ከሚገኘው የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር-03 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር ብቻ/በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከየመንግስት ንብረት ዋጋ ግምትና ሽያጭ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር -02 መግዛት ይችላሉ፡፡
2. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30–6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 –11፡00 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
3. የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ ጥቅምት 11 /2018 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30–10፡30 ሰዓት ድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 12 /2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታው ጥቅምት 12 /2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ5፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በ5፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ መነሻ ዋጋ 20% /ሃያ ከመቶ /የጨረታ ማስከበሪያ C.P.O የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
CPO ለማሰራት
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1 834 0636
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ፊንፊኔ