Your cart is currently empty!
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Sep 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
- የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 1153 እና 011 515 0711 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት |
የቦታው ስፋት በካ.ሜ |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት |
ምርመራ |
1. |
ጄ ኤል ኢ ዋየር እና ኬብል ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
ጄ ኤል ኢ ዋየር እና ኬብል ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
የፋብሪካ ህንጻ እና በዉስጡ የሚገኙ የኤሌትሪክ ገመድና ኬብል ማምረቻ የተለያዩ ማሽነሪዎች (Electric Wire and Cables Manufacturing Machineries) |
10,000 |
31 |
አ/ብ/ክ/መ፣ አንጎለላና ጠራ ወረዳ፣ ጫጫ ከተማ፣ ሰሪቲ ቀበሌ |
ለፋብሪካዉ ህንጻ ብር 36,567,323.39 |
ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም |
4:30-5:30 |
5:30-6:00 |
ንብረቶቹ ተነጣጥለዉ አይሸጡም |
ለማምረቻ ማሽኖች ብር 13,460,693.34 |